እጆቼን በሳሙና እታጠባለሁ፣ ርቀቴን እጠብቃለሁ ፣የጸረ-ኤች.አይ.ቪ ሀኪሜን በስልክ አማክራለሁ፡፡ ረጅሙን ጊዜዬን በቤቴ እንዳሳልፍ ሰዎች በሚበዙበት ቦታ አዘውትሬ እንዳልገኝ የጤና ተቋሜ የ6 ካልሆነም የ3 ወር የጸረ-ኤች.አይ.ቪ መድሀኒቴን በአግባቡ ያቅርብልኝ፡፡ በዚህም ኮሮናን እከላከላለሁ፡፡


  • በአግባቡ የምወስደው የጸረ-ኤች.አይ.ቪ መደሀኒት ኮሮናን ለመከላከል ብርቱ ጋሻ እንደሚሆነኝ መረጃ አግኝቻለሁ፡፡ ዕውቀቱ ለሌላቸው ጓደኞቼ መረጃወን አካፍላለሁ፡፡ ሁላችንም መድሀኒቱን በአግባቡ እየወሰድን የኮሮናን ስጋት እናስወግዳለን፡፡   

የቦርድ ሰብሳቢ መልክት

ትኩረት ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝባቸው ማህበራት!!!!

ኤች.አይቪ/ኤድስ በዓለማችን ብሎም በሀገራችን ላይ ላፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት ያህል  በግልና ቤተሰብ እንደዚሁ በማህበረሰብና በሀገር ላይ በጤና ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ላይ አስከፊ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

መንግስታት ለዚህ ዘርና ቀልም ለማይለየው ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት  ባደረጉት       ርብርብ  እጅግ    በጣም   ጥሩ የሚባል ውጤት አምጥተው ወረርሽኙን ጥሩ በሚባል ደረጃ  ለመቆጣጠር ተችሎ ነበር፡፡ በዚህ ውጤታማ እንቅስቃሴ ውስጥም ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች ሰፊ ድርሻ ማበርከታቸው በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ጉዳይ ነው፡፡

በተለይ በሀገራች የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች በግለሰብ ደረጃ ወደ አደባባይ በመውጣት ትውልድ ይዳን በእኔ ይብቃ በሚል መርህ የምስክርነታቸውን  ቃል  ሠጥተው  ዜጎች ራሳቸውን ከወረርሽኙ እንዲጠብቁ  አድርገዋል፡፡

እነዚህ ኤድስ ላይ የዘመቱ ጀግኖች የችግሩን ስፋት በመገንዘብ ከተበታተነ ይልቅ ባንድ ያበረ ድምጽ  ለውጥ  እንደሚያመጣ  ተረድተው ራሳቸውን በማህበር በማዋቀር ወረርሽኙን ሲዋጉ ቆይተው ማህበራት ክልላዊ ጥምረቶችንና ብሄራዊ  ጥምረትን  ፈጥረው  ማህበረሰቡን ከኤድስ ሲታደጉና ለራሳቸውም መብት ሲታገሉም ቆይተዋል፡፡ ለዚህ ስራ መሳካትም ድጋፍ ሲያደርጉልን የቆዩትን የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ቫይረሱ በደማቸው በሚገኝባቸውና ባንድ ወቅት ማህበረሰቡን ሲያስተምሩ ለነበሩና አሁን በህይወት በሌሉ ጀግኖች የማህበር አባሎቻችን ስም ሳላመሰግን አላልፍም፡፡

ማህበራትና ጥምረቶች ወረርሽኙን  ከመንግስት ጎን ቆመው ከመከላከልና ከመቆ ጣጠር ባሻገር በቫይረሱ ምክንያት እቤት የዋሉ አቅመ ደካሞችንና በዚሁ በሽታ ወላጆቻቸውን ያጡ ችግረኛ ህጻናት የጤናና የኢኮኖሚ ድጋፍ  የሚያገኙበትን የግልና ተቋማዊ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን በመፍጠር የእለት ጉርስ እንዲያገኙና ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ እንዲችሉ አድርገዋል፡፡

ሆኖም እነዚህ ማህበራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመጣው የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ምክንያት በርካታ አባሎቻቸው ከእይታ እየጠፉና የማህበራቱም ንቁ ተሳትፎ እየደበዘዘ መጥቷል፡፡

አሁን እንደ አዲስ እያገረሸ የመጣውን የኤች.አይ.ቪ ስርጭት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በጋራ በተቀናጀ መንገድ ለመመከት የእነዚህ ማህበራት መጠናከር ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ በተበጣጠሰ መልኩ በተለያዩ ክልሎች እየተመደበ ያለው የሁለት በመቶ የኤድስ በጀት ወጥነትና ዘለቄታን በተላበሰ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ማህበራት ተጠናክረው ወረርሽኙን በመግታትም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬን የሚሰጧቸው የተለያዩ ድጋፎች እንዲያገኙ በማድረግ ዳግም ማህበራቱ ወደ ንቁ እንቅስቃሴያቸው የሚመጡበት መንገድ እንዲመቻች የፌደራልንም ሆነ የክልል መንግስታትን በአንክሮ እንጠይቃለን፡፡

መልካም ንባብ

About NEP

The NEP+, formerly known as AELWHA (Association of Ethiopians Living with HIV/AIDS), is established in October 2004 to raise and relay the collective voice of people living with HIV.

GPS Location of NEP+ Office

Contact Us

Address: Mexico Chamber of Commerce building 5th floor.
Phone: +251 111 659 1414/1818/1919
Fax: +251 111 659 1010
P.O.Box: 780 Code-1250
Email: eshetu@nepplus.org / aelwha@ethionet.et