በየጤና ተቋማት የሚሰሩ ኬዝ ማናጀሮች እና የአድሄረንስ ሰፖርተሮች በመንግስት መዋቅር እንዲካተቱ ሃሳብ ቀረበ

የኤች አይ ቪ ስርጭትን በመግታት እቅስቃሴ ውስጥ ላለፉት 11 አመታት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የነበሩት ኬዝ ማናጀሮች እና የአድሄረንስ ሰፖርተሮች አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ዎርክሾፕ በቢሾፍቱ ከተማ ከመስከረም 10 – 11 ቀን፤ 2015 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፤ በውይይቱ መጨረሻም ሰራተኞቹም በመንግስት አስተዳደር ኮሚሽን እንዲታቀፉ ሃሳብ ቀርቀቧል፡፡ በዎርክሾፑ ላይም የኔፕ ፕላስ ቦርድ አባላት ፤የፌድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተወካዮች ፣ የጤና መድህን አገልግሎት ባለሞያዎች ፤ የጤና ሚኒሰቴር ተወካዮች ፤ የክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተወካዮች፤ የየክልል ጤና ቢሮዎች ተወካዮች፤ አንዲሁም የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል፡፡


የዎርክሾፑ ተሳታፊዎች በከፊል
በዎርክሾፑ መክፈቻ ላይ የኔፕፕላስ ተ/ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ጫላ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸውም ኔፕፕላስ ባለፉት 11 አመታት ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለባቸውን ዜጎች በማሰማራት በተለያየ መልኩ ህብረተሰቡን የጠቀመ መሆኑን አስረድተው፤ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ለምሳሌ የሚቀርቡ ናቸው ብለዋል፡፡ አሁንም ሲዲሲ ለዚህ ስራ ይሰጠን የነበረው በጀት ቢያቆምም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አቶ ባይሳ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

በአሁን ወቅት በሃገሪቱ ያለውን የኤች አይ ቪ ሁሄታ በተመለከተ የጤና ሚኒሰቴርን ወክለው ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ ደስታ ሞገስ ሲሆኑ፤ በጽሁፋቸውም በየአመቱ ከ 1ነጥነብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ምክንያትም 680 ሺ ዜጎች ህይወታቸው ያልፋል ብለዋል፡፡ በቀረበው ጽሁፍ እንደተቀመጠው ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ሲሆኑ፤ በዚህም መሰረት 19 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሴቶች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኘ ተገልጿል፡፡ የወንዶችን ቁጥር ስንመለከት ደግሞ 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን ወንዶች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፤ እንደ ጽሁፉ፡፡ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ምክንያት የሚሞቱ ወገኖች ቁጥርን ስንመለከትም በቀላሉ የሚታይ አይደለም ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚሁ ምክንያት በየአመቱ 640ሺ ወንዶች እና 240 ሴቶች ህይወታቸው ያልፋል ብለዋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት በእድሜ ስብጥር ስንመለከተው በ2021 በነበረው መረጃ መሰረት በየአመቱ አድሜያቸው ከዜሮ እስከ 14 አመት የሆነ 150 ሺ ህጻናትና ታዳጊዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ሳቢያም 99ሺ ሕጻናትና ታዳዎች በሞት ይቀጠፋሉ፡፡ በክልል ደረጃ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት በተመለከተም መረጃው እንዳስቀመጠው በ2021 አማራ ክልል፤ ኦሮሚያ እንዲሁም አዲሰ አበባ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ካደረጉት ምክንያቶች መካከልም በተለይ ሴቶች ስለቫይረሱ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤ ኮንዶምን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ጾታን መሰረት ያደረጉ ተግባራት አሁንም ድረስ እየተተገበሩ መሆኑ እንዲሁም የወሲብ ንግድ መስፋፋት ናቸው፡፡
የአቶ ደስታን ማብራሪያ ተከትሎ የኔፕፕላስ ፐሮገራም ማናጀር አቶ ድንቁ ወርቁ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ምንነት እና አስፈላጊነት የሚገልጽ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ በጽሁፋቸውም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በጤና ተቋማት እና በማህበረሰቡ መካከል የሚኖረው አገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በማህበረሰቡ እና በጤና ተቋማት ዘንድ ያለውን ሀብት በአግባቡ አሟጦ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ አብራርተዋል፡፡ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ዋና ዋናዎችም ዜጎች የኤች አይ ቪ ምርመራ እንዲያደርጉ የምክር አገልግሎት መስጠት ፤ ከራሳቸው ተሞክሮ ተነስተው ያለውን ሁኔታ በግልጽ በማስረዳት ቫይረሱ በደማቸው ያለ ዜጎች ህክምና እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም ህክምናውን ያቋረጡ ዜጎች ወደ ህክምናው እንዲመለሱ የተለያዩ ጥረቶችን ማድረግ ተጠቃሾች መኆናቸን አቶ ድንቁ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

የዎርክሾፑ አወያዮች

ሌላው የኬዝ ማናጀሮችና ደሄረንስ ሰፖረተሮች ስራ ያስገኛቸው ውጤቶችና የጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ጽሁፍ ያቀረቡት የኔፕፐላስ ምዘናና ግምገማ ባለሞያ አቶ ቢኒያም ወርቁ ሲሆኑ፤ በጽሁፋቸውም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሚሰሯቸው ስራዎች በርካቶች ቫይረሱ በደማቸው ያለ ዜጎች ህክምናቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እና ህክምና ባለማግኘታች ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን ማስቀረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ለአብነት ያህልም በ2020 እና በ2012 ብቻ ህክምናቸውን ካቋረጡ ከ80ሺ በላይ ወገኖች መካከል ከ40ሺ በላይ የሚሆኑት ወደ ህክምና እንዲመለሱ ማድረግ ችለዋል ብለዋል አቶ ቢኒያም ፡፡በተጨማሪም በኬዝ ማናጀሮች እገዛ እየተደረገላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸው የኤች አይ ቪ ምርምራ እንዲያደርጉ በማሳመን እና ወደ ምርመራ ቦታ በማምጣት ሥራው ላይ እንዲሳተፉ ማድረጋቸውን አቶ ቢኒያም በማብራሪያቸው ገልጸዋል፡፡
የኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖረትሮች የሚሰጡት አገልግሎት በርካታ ቢሆንም፤ ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ የሚደርጓቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸውንም አቶ ቢኒያም አስረግተዋል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች መካከልን እንደ እሳቸው ገለጻ ዋና ዋናዎቹ የምክክር አገሎገሎት ለመስጠት የሚመቹ ገለልተኛ ክፍሎች አለመኖር፤ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰርቪስ ስር ባለመታቀፋቸው ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች ማግኘት አለመቻላቸው፤ ከጤና ተቋማት ደጋፍ በተገቢው መንገድ ማግኘት ነጻ ህኪምና ማግኘት አለመቻላቸው እንዲሁም ዝቅተና ደመወዝ ተከፋይ መሆናቸው እና የፕሮጀከቶች ስራ በጊዜ የተገደበ መሆን ተጠቃሾቹ ናቸው ብሏል አቶ ቢኒያም፡፡
ከየተቋማቱ የመጡ ተሳታፊዎች በየዘርፋቸው 20 የደቂቃ ገለጻዎችን ያደረጉ ሲሆን፤ በዋናነት ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮችም የኤች አይ ቪ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ፤ የኬዝ ማናጀሮች አስፈላጊነት፤ የሚሰሯቸው ስራዎች አንዲሁም ስራዎቻቸውን በሚሰሩበት ወቅት የሚገጥሟቸው ችግሮች አና ችግሮቹን ለመፍታት የተጓዙባቸውን መንገዶች የሚያስረዱ መረጃዎች ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠልም እያንዳንዱ ክልል የየራሱን ተሞከሮ ያቀረበ ሲሆን፤ የአማራ ክልል ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰርቪስ ስር እንዲካከቱ በማድረጉ ችግሩን ከሞላ ጎደል መቅረፍ መቻላቸውን ተወካዩ አስረድተዋል፡፡ ሌሎችም በቀጣይነት ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰረቪሱ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በጤና መድህን ሊታቀፉ የሚችሉበት እና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት በሚቻልበት መንገድ ላይም ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ ከኢትጵያ ጤና መድን አገልግሎት ተወካይ አቶ ጉደታ አበበ በአሁኑ ወቅት ያለውን የጤና መድን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ እንደ አቶ ጉደታ ማብራሪያ የጤና መድን አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ መዳረሱ እንደ ግዴታ ሊወሰድ ስለሆነ ማንም ከዚህ አገልግሎት ውጪ ሊሆን አይችል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉም ዜጋ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አሊያም በማህበራዊ ጤና መድህን እንዲታቀፍ የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ሥለሚደረግ በዚህ ሂደት ውስጥ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ዜጎችም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አቶ ጉደታ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በተለይ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ረገድ ያላቸው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ በሲቪል ሰርቪሰና በጤና መድን ስር ታቅፈው አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ እና እያንዳንዱም የየራሱን ሃላፊነት ለመወጣት ቃል በመግባት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

አድሎና ማግለል ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭሰ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) በመድሎና ማግለል ላይ
ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጋር ውይይት አካሄደ
ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) በኤች
አይ ቪ ምክንያት በሚደርሰው አድሎና ማግለል ላይ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ
ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴጋር ነሃሴ 2 ቀን 2014 በቢሾቱ ኪሎሌ ሆቴል ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይም የተለያዩ አካላት ንግግር አድርገዋል፡፡


የውይይቱ ተሳታፊዎች በከፊል

በውይይቱ ቋሚ ኮሚቴውን በመወከል ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ሲሆኑ፤
እሳቸውም በገለጻቸው በኤች አይ ቪ ተጽእኖ ላይ እንዲህ አይነት በቁጥር ላይ የተመሰረተ
ጥናት መቅረቡ በጉዳዩ ላይ የበለጠ ስራዎችን ለመስራት የሚኖረው ጠቀሜታ የላቀ መሆኑን
አብራርተዋል፡፡ በግምት ብቻ የሚሰሩ ስራዎች የተፈለገውን ውጤትለማስገኘትም ሆን
በህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል
ብለዋል ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ፡፡ በዚህ መልኩ ተጨባጭነት ያለው ጥናት መደረጉ በጉዳዩ
ላይ የበለጠ ለመስራት የሚፈልግ ሌላ አካል እንኳን ቢኖር ጥሩ መነሻ የሚሆንና
በማህበረሰቡ ውስጥም ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑን ወ/ሮ ወርቅሰሙ ጨምረው
ገልጸዋል፡፡


ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ
ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወክለው የመጡት ወ/ ሮ ምርቴ ጌታቸው በበኩላቸው ሚኒስቴር
መስሪያ ቤቱ የኤች አይ ቪ ስርጭት አና የሚከሰቱት ተያያዥ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ
ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ እንዲህ አይነት ጥናቶች መካሄዳቸው ስራውን የበለጠ
ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል፡፡ ባለፉት አመታት በኤች አይ ቪ
ምክንያት የሚከሰት ሞትን በ 53በመቶ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት 87 በመቶ መቀነስ
ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ምርቴ፤ የኤች አይ ቪ ህክምና ሽፋኑ 93 በመቶ እንዲሁም ቫይረሱን
የመቆጣጠር አቅም ወደ 96 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ተወካዩዋ፡፡ ተመርምሮ
ራስን ማወቅን በተመለከተም በአሁኑ ወቅት 84 በመቶ የሚሆኑት ወገኖች ተመርምረው
ውጤታቸውን ያወቁ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ 16 በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ ምክንያቶች
ምርመራ እንዳላደረጉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ተመርምረው ራሳቸውን እንዳያውቁ
ከሚያደርጓቸው ምክንያያቶች መካከልም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊደርስባቸው
የሚቸለውን መድሎና መገለል በመፍራት መሆኑንም አብራርተዋል ፡፡ በአሁኑ ሰአትም ከ
1500 በላይ የሚሆኑ የኤች አይ ቪ ህክምና መስጫ ጣቢያዎች እንዲሁም ከ4000 በላይ የ
ኤች አይ ቪ የምርመራ ጣቢያዎች እንዳሉም አብራርተዋል ወ/ሮ ምርቴ፡፡


ወ/ሮ ምርቴ ጌታቸው

እንግዶች ያደረጉትን ንግግር ተከትሎም የጥናቱን አስፈላጊነት፤ አላማ እና አካሄድ
በተመለከተ የኔፕ ፕላስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የጥናቱ የቴክኒክ ኮሞቴ ሰብሳቢ አቶ
ጌታቸው ጎንፋ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ጥናቱን ማድረግ የተፈለገበት
ምክንያት በኤች አይ ቪ ምክንያት የሚደርስ መድሎና መገለል ያለበትን ደረጃ አና ሁኔታ
ለማውቅ ፤ በመድሎና መገለል እና በኤች አይ ቪ አገልግሎት መካከል ስላለው ግንኙነት
ለመገምገም እንዲሁም በመድሎና መገለል ምክንያት የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽእኖ ማቃለል
በሚቻልበት ሁንታ ላይ ምክረ ሃሳብ ለማስቀመጥ እንደሆነ አቶ ጌታቸው በገለጻቸው
ጠቁመዋል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱን ለማድረግም የተለያዩ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮ እንደነበረ እንዲሁም
በሂደቱ የተለያዩ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ዘዴዎች መከተላቸውን ገልጸዋል፡፡ ጥናቱ
ደረጃውን የጠበቀ እና ተአማኒነት ያለው እንዲሆንም በዘርፉ ልምድ ያላቸው የጥናት ተቋማት
ያስቀመጧቸውን ያሰራር ሂደቶች በመመልከት እና በመከተል መሰራቱም በመድረኩ
ጨምረው አብራርተዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ጎንፋ
በመቀጠልም የጥናቱ ቴከኒካል ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩዬ
ዳመጠው አጠቃላይ የጥናቱን ውጤት ጠቅለል ባለ መልኩ አቅርበዋል፡፡ በማብራሪያቸወም
ከጠናቱ ተሳታፊዎች መካከል ምን ያህሉ የኤች አይ ቪ ውጤታቸውን ለሌሎች አካላት
አሳውቀዋል በሚል የጀመረው የወ/ሮ ጥሩዬ ገለጻ፤ በዚህ ጥናት ላይ ከተሳተፉ ሰዎች መካክል
84 በመቶዎቹ የኤች አይ ቪ ውጤታቸውን ቢያንስ በአካባቢያቸው ለሚገኝ አንድ ሰው
መግለጻቸውን ያመለክታል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 16 በመቶ የሚሆኑት የኤች አይ ቪ
ውጤታቸውን ለማንም ሰው ያልገለጹ መሆናቸውን ምክትል ሰብሳቢዋ አክለው ገልጸዋለ፤፡፡
በተጨማሪም 23.4 በመቶዎቹ የጥናቱ ተሳታፊዎች የ ኤች አይ ቪ ውጤታቸው
ያለፍቃዳቸው የተገለጸባቸው ፤ 19.7 በመቶዎቹ ደግሞ የ ኤች አይ ቪ ውጤታቸውን
ያሳወቁት በተለያዩ ምክንያቶች ተገደው እንደሆነ የጥናቱ ተሳታፊዎች መግለጻቸውን
አብራርተዋል፡፡ ውጤታቸውን ይፋ እንዲያደርጉ ያሰገደዷቸው ነገሮችም የፍቅር እና የትዳር
ጓደኛ ለመያዝ፤ የተለያዩ እገዛዎችን ለማግኘት አና ለመሳሰሉት ምክንያት እንደሆነ የጥናቱ
ተሳታፊዎች አብራርተዋለ፡፡

ወ/ሮ ጥሩዬ ዳምጠው
የቀረበው መረጃ እንደሚጠቁመው በ ኤች አይ ቪ ምክንያት የሚመጣ መድሎና
መገለል ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ዜጎች ላይ አዎንታዊ አና አሉታዊ ተጽእኖዎችን
ያስከትላል፡፡ 45 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹትም በኤች አይ ቪ
ውጤታቸው ምክንያት የደረሰባቸው መድሎና መገለል በሕይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ
አሳደሮባቸዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደገለጹትም በተደረገባቸው መድሎና መገለል ሳቢያ በራስ
መተማመናቸውን እንዲያጡ፤ ጭንቀትን መቋቋም እንዲያቅታቸው ብሎም የፍቅር ጓደኛ
እንኳን መያዝ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ልጅ ለመውለድ
የነበራቸውን ተስፋ እንዳሳጣቸው ገልጸዋል ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 44 በመቶ
የሚሆኑት ተሳታፊዎች በ ኤች አ ይ ቪ ውጤታቸው ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው
መድሎና መገለል የበለጠ በራሳቸው አንዲተማመኑ በማድረግ፤ ጭንቀታቸውን እንዲቋቋሙ
በማገዝ እንዲሁም ጠንካራና ተስፈኛ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ በአዎንታዊ መንገድ
እንደረዳቸው ተጠቁሟል፡፡
የጥናት ውጤቱ አጠቃላይ ዳሰሳ ከቀረበ በኋላም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አና
አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፤ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያዎች ከአቅራቢዎች
ተሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ተሳታፊዎች የየራሳቸውን አስተያያት አና ጥቆማ በመስጠት እና
ሰፊ ውይይት በማድረግ የውይይት መድረኩ ተጠቃሏል፡፡

የኔፕ ፕላሰ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

የኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) 17ኛ
መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ግንቦት 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ከረዩ ሂል ሪዞርት
ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የኔፕ ፕላስ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ጫላ ባደረጉት ንግግር፤
ኔፕ ፕላስ ላለፉት 17 አመታት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት ከ200 ሺህ በላይ ቫይረሱ
በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በማህበር ተደራጅተው አድሎና መገለል እንዲቀንስና ለሀገራዊ
ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ፤
ማህበረሰቡም ራሱንና ቤተሰቡን ከወረርሽኝ እንዲጠብቅ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ራሳቸውን
ይፋ በማውጣት ትምህርት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ 2030 ሊደርስበት ያስቀመጠውን የ 95 ፤ 95 ፤ 95 እቅድ
ተግባራዊ ለማድረግ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ከጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ጋር
እንዲቆራኙ ወይም የህክምና ክትትላቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም መድሃኒቱን ጀምረው
ያቋረጡ ወገኖች በአፋጣኝ ወደ ህክምና ክትትል እንዲመለሱ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ
ይገኛል ብለዋል አቶ ባይሳ፡፡
የኔፕፕ ፕላስ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብድርሃማን ከማል በበኩላቸው፤ ለአዲሱ
የግሎባል ፈንድ ውድድር በቂ ዝግጅት በማድረግ ውጤታማ ሆኖ ለማሸነፍ መቻሉን
አብራርተዋል፡፡ ከአለፈው ጠቅላላ ጉባዔ ወዲህ ባለው ስራቸው ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን
ሰብሳቢው ሲገልጹም ፤ ወቅቱን ያልጠበቀ የሲዲሲ በጀት መቋረጥ፤ በርከት ያሉ ሰራተኞች
ስራቸውን መልቀቅ እና የበጀት እጥረት ዋናውናዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡ እነዚህን
ቸግሮችም በተለያየ መልኩ ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውን ሰብሳቢው ጨምረው
ገልጸዋል፡፡ የስራ አመራሮችን በተመለከተም የአመራርነት ሃላፊነታቸውን ያልተወጡትን
የብሄራዊ ጥምረቱ ስራ አስኪያጅ በአዲስ ተወካይ ቦርዱ መተካቱን ሰብሳቢው ጨምረው
ገልጸዋል፡፡
የበመቀጠል ጠቅላላ ጉባዔው የተጓደሉ እና ጊዜያቸውን የጨረሱ የጠቅላላ ጉባዔ
አመራሮች ምርጫ በህገ ደንቡ መሰረት አካሂዷል፡፡ ጉባዔው በሶስቱ አስመራጭ ኮሚቴ
አባላት አማካይነት አዲስ አመራሮችን የመረጠ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት አቶ ማሙሸ ንጉሴ
የጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢ ፤ወ/ሮ እቴነሽ እሸቴ የጠቅላላ ጉባዔ ም/ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ሙሴ
ማማጫ የጠ ቅላላ ጉባዔ ጸኃፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በተጨማሪም በድርጅቱ በቦርድ አባልነት ከሀረሪ ክልል፤ ከአዲስ አበባ እና ከሴቶች
ጥምረት የተወከሉትን 3 የክልል ተወካዮችን ጉባዔው በቦርድ አባልነት እንዲሰሩ ጉባዔው
ያጸደቀ ሲሆን፤ በተገጓደሉ ጠቅላላ ጉባዔ አባልነትም የጋመቤላ ክልል ወክሎ የላከው 1፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የላካቸው 2 እና ሴቶች ጥምረት የላካቸው 4 ተወካዮችን
አጽድቋል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔው በመቀጠልም በ2021 የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር የገመገመ ሲሆን፤
በመጀመሪያ የስራ አመራር ቦርዱን ሪፖርት በዝርዝር አይቷል፡፡
በቦርዱ ሪፖርት ላይ ከአባላት የተለያዩ ጥያቄናዎችና አስተያቶች የተነሱ ሲሆን፡
ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶችም የቦርዱ ሰብሳቢው ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ሰብሳቢው
በምላሻቸውም የተቋረጠውን የሲዲሲ ፕሮጀክት በተመለከተ ፕሮጀክቱን ለመመለስ ጥረት
እንደሚደረግ፤ የኔፕ ፕላስ በጀት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ በመሆኑ የድርጅቱ መመሪያዎችና
ደንቦችን በዚያ መልኩ እንደሚቃኝ አስረድተዋል ፡፡ የግሎባል ፈንድ አሰራሩ በአጠቃላይ
ስለተቀየረ የበጎ ፈቃደኞችን እና ሌሎች ሰራተኞችን አለማካተቱን የገለጹት ሰብሳቢው፤
በተጨማሪም በጦርነት የተጎዱ ክልሎችንና ሌሎች ድጋፍ የሚፈልጉ ማህበራትን ለመደገፍ
ቦርዱ ከ ጽ/ቤቱ ጋር የጋራ እቀድ አቅዶ እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ቦርዱ
ስራውን በአግባቡ እያከናወነ መሆኑን የተገነዘበ ሲሆን ፤ ለሚቀጥለው አመት የሃብት ማበልጸግ
ስራ እንዲሁም የውጪ የቦርድ አባላትን የማካተቱ ስራ ትኩረት ተሰጠቶ እንዲሰራ የውሳኔ
አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡
ቀጥሎ ለጠቅላላ ጉባዔው የጽ/ቤቱ የ2021 ሪፖርት በክትትልና ምዘና መምሪያ ሃላፊው
በአቶ በላይ ረታ የቀረበ ሲሆን ፤ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ በላይ
ማብራሪያ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ከ 150 ሺህ በላይ ለሆኑ ቫይረሱ በደማቸው ላለባቸው
ወገኖች በጸረ ኤች ኤቪ ህክምና ቁርኝት፤ በቫይረስ መጠን ልኬት ፤ በጸረ ኤች አይቪ ህክምና
ቅድመ ዝግጅት፤ ቤተሰብና የጾታ አጋሮቻቸውን በማስመርመር ፤ ከኮቪድ 19 በመከላከል እና
በአጠቃላይ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ድጋፍ እንደተሰጣቸው ተብራርቷል፡፡
ከቀረበው ሪፖርት መረዳት እንደተቻለውም ድርጅቱ በኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነስ እና
መድሎና መገለል እንዲቀንስ በማድረግ እንዲሁም ከጸረ ኤች አይቪ መድሃኒት ጋር ያለውን
ቁርኝት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡
አባላቱ ሪፖረቱ ካደመጡ በኋላም ፈንድ ለማግኘት ከመንግስት ጋር ያለው ቁርኝት ምን
ይመስላል፤ እንዲሁም የኔፕ ፕላስ የ 5 አመት መሪ እቅድ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ የሚሉና
የመሳሰሉ ጥቄዎችን አንስተዋል፡፡ ለጥያቄዎቹም ከድርጅቱ ጽ/በት ማብራሪያዎች
ተሰጥተዋለ፡፡
በተጨማሪም የኔፕ ፕላስ የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተገምግሞ መጠናቀቁን
እና ሴቶችና ሴቶች ጥምረትን ለማገዝ በጽ/ቤቱ በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም
ተብራርቷል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ጠቅላላ ጉባዔው የ2022 እቅድን ያደመጠ ሲሆን አባላቱም ግሎባል ፈንድ
ፈጻሚ ያልሆኑ አባላት ጉዳይ በእቅዱ ቢካተት፤ በጦርነት የተጎዱ ማህበራትና ሴቶች በተለየ
መልኩ የሚደገፉበት መንገድ ቢመቻች በማለት አሳስበዋል፡፡ጠቅላላ ጉባዔው ሪፖረቱንና
እቅዱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባዔው የ2021 የውጭ ኦዲት
ሪፖረተን ካደመጠ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

NEP+ Provided Refresher training for Case managers and adherence Supporters

(February 26 2022 Pr and Communication Department)

NEP+ Provided refresher training for 814 ( male 199 and female 615) case managers and adherence support drawn from dsellected health facilities found in SNNP, Sidama, South west , Oromia, Gambella Regions and Addis Ababa City Administration.
According to the information from NEP+ program Department, the training was focused on Mental Health Illness screening, Cervical Cancer ,prevention, key messages on viral Undetected leads to Un transmitted HIV during sexual intercourse and finally on the revised data management tools. The training was given in 6 round for 2 days each
The training was given at Adama, Jimma, Bishoftu and Butt Jira Towns within three month time from December 2021 to February, 2022.

Trainees in partial.
Trainees in partial.

Sample Text

ኔፕ ፕላስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት አካሄደ

ኔፕ ፕላስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት አካሄደ ኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) 16ኛ መደበኛ
ጠቅላላ ጉባኤውን በባህርዳር ከተማ ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው ሲሆኑ በንግግራቸው ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሶስት 90ዎች ፕሮግራም ወደ ሶስት 95ቶች መለወጡን አስታውሰው በተለይ በአሁኑ ሰኣት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን 95 ለማሳካት ሰፊ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት ይህ ታላቅ ጉባኤ መካሄዱ ለፕሮግራሙ መሳካት ሰፊ አበርክቶ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ታሪኩ በላቸው የአማራ ክልል ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አያይዘውም ዓለምን እየፈተነ ያለው የኮቪድ 19 ወረርሽን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዘመቻ አስቸጋሪ እንዲሆን እያደረገው ካሉ በኋላ በኢኮኖሚ ጠንካራ ያልሆኑና አንስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ሴቶች እህቶቻችን የኮሮና ወረርሽኝ ኑሯቸውን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል፡፡

በተለይ ይህ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት እንዲጨምር በማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ እንዳለም የሚያመለክቱ መረጃዎች እንዳሉ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ምክትል ቢሮ ኃላፊው በንግግራቸው መጨረሻም ጉባኤው በእቅዶቻቸው ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመከላከል ስራን እንዲካትቱ ጥሪ አድርገው የአማራ ክልል መንግስት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመከላከል ረገድ ለሚደረጉ ጥረቶች አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ድጋፍ ለመስጠት ከክልሉም ሆነ ከብሄራዊ ጥምረቱ ጎን እንደሚቆም ቃል በመግባት ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን አገባደዋል፡፡ ከመክፈቻው ንግግር ቀደም ብሎ የኔፕ ፕላስ ዋና ስራ አስኪጅ ለተሰብሳቢዎቹ ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ኔፕ ፕላ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት በርካታ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በንግግራቸውም ኔፕ ፕላስ ከሲዲሲ እና ከግሎባል ፈንድ ውጪ ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብና የአይነት እንደዚሁም የቴክኒክ ድጋፎች ማገነቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ ለደርጅቱ ችግር ሆኖ የመጣው መላው አለምን ፈታኝ የሆነው የኮቪድ 19 ክስተት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ መኮንን አለሙ የኔፕ ፕላስ ዋና ዳይሬክተር ለጉባኤተኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ሲያደርጉ ይህንኑ ወረርሽኝ ለመከላከልም ኔፕ ፕላስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ የእጅ ማጽጃና የፊት መሸፈኛ ማስኮችን በድጋፍ መልክ ማግኙቱን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እድላም ገ/ስላሴ በበኩላቸው ቦርዱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መደበኛ እና አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማካሄድ የኔፕ ፕላስ የስራ ግምገማ በማድረግ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ አቅጣጫዎችና የቅርብ ድጋፍ ሲያደርግለት መቆየቱን አስታውሰው ከዚህ ውጭ በአንዳንድ የክልል ጥምረቶች ላይ በታዩ ችግሮች ላይ በቦታው ድረስ በመገኘት የመፍትሄ ሀሳቦችን ተሰጥተዋል ብለዋል፡፡ አቶ እድላም ገ/ሥላሴ የኔፕ ፕላስ ቦርድ ሰብሳቢ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በሶስት ቀናት ቆይታቸው የድርጅቱን የቦርድ ሪፖርትና እቅድ፣ የጽቤቱን ሪፖርትና እቅድ፣ የኦዲት ሪፖርት እና አዲሱን የመተዳደሪያ ደንብ አጽድቋል፡፡

ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ)

ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች
አይቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ
(ኔፕፕላስ)

  • ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ለመከላከልና
    ለመቆጣጠር የበጎ ፈቃደኞች ስንቅ
    ሀ/ መግቢያ
    ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በአለም ላይ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የበርካታ
    ሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉም በተጨማሪ ዛሬም ድረስ በርካታ ዜጎች
    ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅትም
    የሚከተሉት እውነታዎች ይስተዋላሉ፡፤
    1. ይህ ወረርሽኝ አሁንም በአለም ላይ ዋንኛ የጤና ችግር
    ሲሆን ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እንደ እ.አ.አ ዲሴምበር
    2018 መጨረሻ ድረስ ከ32 ሚሊዮን ህዝብ በላይ
    ህይወት እንደሳጣ እና ከ37.9 ሚሊዮን ህዝብ በላይ
    ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡
    2. በአለም አቀፍ ደረጃ በተሰጠው ትኩረት ምክንያት
    በሽታውን የመከላከሉና የመቆጣጠሩ ስራ እንዲሁም
    አገልግሎቶችን የማዳረሱ ሥራዎች በጥራታቸውም ሆነ
    በስፋት እየተሻሻሉ በመምጣታቸው በአጠቃላይ ቫይረሱ
    በደማቸው ከሚገኝባቸው ሰዎች መካከል እ.አ.አ.
    በ2018 ብቻ ከአዋቂዎች መካከል 62% ከህጻናት
    መካከል ደግሞ 54% ዕድሜ ልክ በሚወሰደው የጸረ ኤች
    አይ ቪ ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የተቻለ
    ሲሆን ጥረቶቹ ዛሬም እንደ ቀጠሉ ናቸው፡፡
    በመጠቀም ምርመራ የሚያስፈልጋቸውን ተጋላጭ ግለሰቦችን
    ለይቶ ማወቅ፤ከዚያም ማስመርመር
    1.2. ቤት ለቤትና መስክ ላይ የተንቀሳቃሽ የኤች.አይ.ቪ
    ምርመራ አገልግሎት ማካሄድ
    ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች የትዳር ወይም
    የወሲብ አጋርን ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መለየትና
    ማስመርመር፣
     ኤች.አይ.ቪ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጡ ሰዎቸ
    የቲቢ እና የአባለ-ዘር በሽታ ምርመራ እንዲያደርጉ
    ማበረታታትና እንዲመረመሩ ማድረግ ፤
     ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናት ወይም
    ልጆች የኤች.አይ.ቪ ምርመራ እንዲያደርጉ ማድረግ
     ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸውን ለድጋፍ፣ እንክብካቤና
    ለሕክምና ወደ ጤና ተቋማት መላክ
     በሚታዩቱ የህመም ምልክቶች ላይ በመመርኮዝ የቲቢና
    የአባለ-ዘር በሽታ ተጠርጣሪዎችና ታማሚዎችን መለየትና
    ወደ ጤና ተቋማት በመላክ ማስመርመርና ማሳከም፡፡
    2. 2ኛና 3ኛውን 90 ተግራዊ ለማድረግ ሊሰሩ የሚገቡ
    ሥራዎች
    2ኛና 3ኛውን 90 ተግባራዊ ለማድረግ የማህበረሰብ የኤች.አይ.ቪ
    እንክብካቤና ሕክምና በቀጥታ የሚገኙ አገልግሎቶችን ተግባራዊ
    ማድረግ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
     በአከባቢው ስለሚገኙ የኤች.ኤይ.ቪ መከላከያና
    መቆጣጠሪያ ሥራ አገልግሎቶችን በተመለከተ የህብረተሰቡ
    ግንዛቤ እንዲዳብር ማድረግ፣
     የከፍተኛ ድብርት ተጠቂ የሆኑትን እንዲሁም አደንዛዥ/
    አነቃቂ ለምሳሌ ሲጋራ፤የተለያዩ የሀሺሽ አይነቶችን፤ጫት
    ወዘተ… ተጠቃሚዎችን ፤ መለየትና ከችግሩ እንዲወጡ
    ማገዝ፤ ማበረታታት
     የስነ-ምግብ ዳሰሳ በማካሄድ በምግብ አጠቃቀም ላይ
    ምክክር ማካሄድ
     የንፁሕ ውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ምክክር ማካሄድ
     ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች የግል
    እንዲሁም የአከባቢያቸውን ንፅሕና እንዲጠብቁ መርዳትና
    ማበረታታት
     አካባቢያቸው ወባ ያለበት ከሆነ እራሳቸውን ከወባ በሽታ
    እንዲከላከሉ መምከር የመከላከያ ዘዴዎችን የሚማሩበትን
    ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
     ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ በሚረዱ ስልቶች ላይ
    ምክክር ማካሄድ
     ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍልን ማዕከል
    ያደረገ ኮንዶም የማስተዋወቅ ሥራ መሥራትና ኮንዶም
    በማሰራጨት በአግባቡ እንዲጠቀሙ የምክርና የትስስር
    ወይም የቅብብሎሽ አገልግሎት መስጠት
     የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምና ጥቅም ላይ ግንዛቤ ለማዳበር
    ተጠቃሚውን ማስተማር
     የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምና ዘለቄታዊ ቁርኝትን ለማበረታታት
    በተጠቃሚው ፈቃደኝነት ላይ በመመርኮዝ የቤት ለቤት
    ጉብኝት ማካሄድ
     የአቻዎች ደጋፊ ቡድኖችን በተጠቃሚው ቅርበትና ምቾት
    ላይ በመመርኮዝ ማቋቋም፤ በአስፈላጊ ቁሳቁስ ማደራጀትና
    ማጠናከር
     የአቻ ቡድኖች በየጊዜው የውይይት ዕቅድና መድረክ
    እንዲኖራቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ የመወያያ ርዕሶች
    እንዲኖራቸው ማድረግ፤ በውይይት ወቅት ያላግባቡአቸው
    ነጥቦች ላይ በባለሙያ ማብራሪያ እንዲቀርብባቸው
    ሁኔታዎችን ማመቻቸት
     የተጠቃሚው ገቢ እንዲያድግ የአካባቢ/ የመንደር ቁጠባና
    ብድር ቡድኖችን ማቋቋምና ድጋፍ መስጠት ከጥቃቅንና
    አነስተኛ ሥራዎችና ከመሳሰሉት ጋር ማገናኘት
    ይሁን እንጂ የሚሰጡ አገልግሎቶች በቂ ካለመሆናቸው የተነሳ
    ከላይ በተጠቀሰው አመት ብቻ ከአለም ህዝቦች መካከል
    770 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታና ተያያዥ በሆኑ ችግሮች
    የተነሳ ለህልፈት እንደተዳረጉ መረጃዎች ያሳዩ ሲሆን 1.7
    ሚሊዮን ዜጎች በአዲስ መልክ እንደ ተያዙም ተገምቷል፡፡
    4. በአገራችንም እንደ የኢትዮጵያ ጤና ምርምር እንስቲትዩት
    ትንበያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2020 ብቻ
    745719 ኤች ኤይ ቪ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች
    ሊኖሩ እንደሚቺሉ የተተነበየ ሲሆን በዚሁ አመት 8426
    ሰዎች ከዚሁ በሽታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ህይወታቸውን
    ሊያጡ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 21609
    ሰዎች አዲስ በቫይረሱ እንደሚያዙም ግምቱ ያስረዳል፡፡ ከዚህ
    በተጨማሪ ከፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ
    ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው በአሁኑ ወቅት
    የኤች.አይ.ቪን ስርጭት 75% መግታት ሲገባን መግታት
    የተቻለው ግን 52% ብቻ ነው፡፡ ቫይረሱ በደማቸው፡፡
    ከላይ ከተጠቀሱት መረጃዎች የምንረዳው ምንም እንኳ
    ኤች.አይ.ቪ ኤድስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ
    መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም በርካታ ሥራዎችን መሠራት እንዳለብን
    ነው፡፡ በተለይም በህብረተሰብ ደረጃ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ
    ስራዎችን መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ ህብረተሰቡን ለማሳተፍ ደግሞ
    በጎ ፈቃደኞቸን በመመልመል፤ ማሰልጠንና በማንቀሳቀስ መሠረታዊ
    የኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ሥራን በትኩረት እና ውጤት
    ማምጣት በሚችል መልኩ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ በጎ ፈቃደኞችም
    በአግባቡ ሥራቸውን አውቀው መስራት ያመቻቸው ዘንድ ይህ የበጎ
    ፈቃደኞች ሥንቅ ተብሎ የተሰየመ ጹሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡
    ለ/ በኤች.አይ.ቪ መከላከል ሥራ ውስጥ በጎ ፈቃደኛ
    ማን ነው?
    በጎ ፈቃደኛ ማለት በፈቃዱ ያለማንም አስገዳጅነት ጉልበቱን፤
    ጊዜውንና ገንዘቡን በማበርከት በኤች አይ ቪ ወይም በሌላ በሽታ
    የተያዘ ወይም ተያያዥ በሆኑ በሽታዎች ምክንያት የታመሙ ወይም
    ሊታመሙ የሚችሉ ሰዎች ችግሩን እንዲቋቋሙ በተለያየ መንገድ
    ድጋፍ የሚያደርግና የሚያበረታታ ወይም የሚረዳ ግለሰብ ፤ ቡድን
    ወይም ድርጅት ነው፡፡ ድጋፉ የሚሰጠውም በግለሰብ ደረጃ ወይም
    ከድርጅት ጋር በመተባበር ሊሆን ይችላል፡፡
    ሐ/ በጎ ፈቃደኛው ምን ምን እንዲሠራ ይጠበቃል
    የ 90-90-90 ዕቅድን ባለንበት አከባቢ ሁሉ ተግባራዊ እንዲሆን
    መስራት
    90-90-90 ማለት
     የመጀመሪያው 90 ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ
    ይኖርባቸዋል ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች መካከል 90%
    የሚሆኑ ተመርምረው ውጤታቸውን እንዲያውቁ ማድረግ፤
     2ኛው 90 ኤች.አይ.ቪ በደማቸው እንዳለባቸው
    ከተረጋገጠው ሰዎች መካከል 90% የሚሆኑት የፀረኤች.አይ.ቪ መድኃኒት እንዲወስዱ ማድረግ፤
     የመጨረሻው 90 የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት
    ከሚወስዱ ሰዎች መካከል 90% የሚሆኑ በደማቸው
    ውስጥ ያለውን የቫይረሱን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ
    ናቸው፡፡
    1. የመጀመሪያውን 90 ተግባራዊ ለማድረግ
    የሚከተሉን የምርመራ ዘዴዎች በመጠቀም ሥራ መስራት
    1.1. ማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ
    እንዲካሄድ ማድረግ
     በአከባቢው ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ፣
    ባል ወይም ሚስት የሞተባቸውንና የተፋቱ ባለ ትዳሮችን
    መለየትና በመመዝገብ ወደ ጤና ተቋም በመላክ
    ማስመርመር
     ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑና ቤተሰቦቻቸው በደማቸው
    ውስጥ ኤች.አይ.ቪ ያለባቸውን ህጻናት/ልጆች መለየት
    እና ወደ ጤና ተቋማት መላክና ማስመርመር
     የማህበረሰብ ድጋፍና እንክብካቤ ጥምረትን
    (community Care coalition)
    ማግለልና አድልዎን ለመቀነስ ባህሪ-ተኮር የግንዛቤ
    ማዳበሪያ ሥራዎችን መሥራት
     ለተጎጂዎች የስነልቦናዊ ድጋፍ መሥጠትና
    እንደየእምነታቸው መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ማበረታታት
     ከህክምና ክትትል የጠፉ ታካሚዎችን መፈለግና ወደ
    ህክምና መመለስ እና ደግመው እንዳያቋርጡም በሚገባ
    መምከር፤ ማገዝ፡፡
     በሰውነት ውስጥ ስለሚኖረው ቫይረስ መጠንና ስርጭት
    (CD4 and viral load) ክትትልና ምርመራ
    እንዲያደርጉ ማስተማርና በየጊዜው በፕሮግራም
    እንዲመረመሩ ማድረግ
     ዋና ዋና የጸረ-ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶችን
    መለየትና ተጠቃሚዎቹ እንዲያውቁት ማድረግ
     የማህበረሰብ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ህክምና
    አሰጣጥ ሞዴልን በሚሰጡ መመሪያዎች ላይ በመመርኮዝ
    ተግባራዊ ማድረግ
    መ/ የተሠራውን ሥራ መመዝገብ
    በመጨረሻም የሠራነውን ሥራ መመዝገብና ለሚመለከተው አካል
    ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ አስተባባሪ ድርጅት የራሱ
    የሆነ መረጃ መመዝገቢያና ሪፖርት ማድረጊያ ቅጾች አሉት፡፡ በዚህ
    መልኩ የተሰሩትን ሥራዎች በቅጾቹ መሠረት መዝግቦ ሪፖርት ማድረገ
    ይጠበቃል፡፡
    NEP+
    Tel. +251 116 591 919 / 1818
    P.O. B 789 code 1250
    www.facebook.com/nepplus.nepplus,
    www.nepplus.org, face book Page
    www.facebook.com/Network-of-Networks-of-HIV- Positives-in-Ethiopia

አሁንም ትኩረት ለኤች.አይ.ቪ መከላከል

ጥምረት / TIMRET

የዓለም የኤድስ ቀን በአፋር ክልል በድምቀት ተከበረ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ የዓለም ኤድስ ቀን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ታህሳስ
12 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ
ውሏል፡፡

  1. በጎ አድራጎት ማህበራት በሀገር አቀፍም ሆነ
    በአካባቢ መዋቅር ላይ በፕሮግራም ቀረጻ ፣
    አፈጻጸም. በምዘናና ክትትል ስራ ላይ በመሳተፍ
    ትርጉም ያለው ተሳት እንዲኖራቸው ሁኔታዎችን
    ማመቻቸት
  2. የሀገር ውስጥ ሀብትን ለመጠቀም የሚያስችል
    የአሰራር ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ
    በተለይም ተከማችቶ የሚገኘውን የኤድስ ፈንድ
    ጥቅም ላይ ለማዋል በመንግስት በኩል የህግ
    መሰረት እንዲፈጠር መስራት የሚሉ የወደፊት
    አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ስብሰባው
    ተጠናቋል፡፡
    ቅጽ 6 ቁጥር 1 ጥር 2012 ጥምረት / TIMRET Volume 6 Issue 1 Feb. 2020
    7

    Your ClipBoard is currently empty. Please copy row or element before pasting!

    እጆቼን በሳሙና እታጠባለሁ፣ ርቀቴን እጠብቃለሁ ፣የጸረ-ኤች.አይ.ቪ ሀኪሜን በስልክ አማክራለሁ፡፡ ረጅሙን ጊዜዬን በቤቴ እንዳሳልፍ ሰዎች በሚበዙበት ቦታ አዘውትሬ እንዳልገኝ የጤና ተቋሜ የ6 ካልሆነም የ3 ወር የጸረ-ኤች.አይ.ቪ መድሀኒቴን በአግባቡ ያቅርብልኝ፡፡ በዚህም ኮሮናን እከላከላለሁ፡፡

    
    

    • በአግባቡ የምወስደው የጸረ-ኤች.አይ.ቪ መደሀኒት ኮሮናን ለመከላከል ብርቱ ጋሻ እንደሚሆነኝ መረጃ አግኝቻለሁ፡፡ ዕውቀቱ ለሌላቸው ጓደኞቼ መረጃወን አካፍላለሁ፡፡ ሁላችንም መድሀኒቱን በአግባቡ እየወሰድን የኮሮናን ስጋት እናስወግዳለን፡፡   

    About NEP

    The NEP+, formerly known as AELWHA (Association of Ethiopians Living with HIV/AIDS), is established in October 2004 to raise and relay the collective voice of people living with HIV.

    GPS Location of NEP+ Office

    Contact Us

    Address: Mexico Chamber of Commerce building 5th floor.
    Phone: +251 111 659 1414/1818/1919
    Fax: +251 111 659 1010
    P.O.Box: 780 Code-1250
    Email: eshetu@nepplus.org / aelwha@ethionet.et