(ኔፕ ፕላሰ ፕአር ኤንድ ኮሙንኬሽን አዲስ አበባ ጥር 22 2017))
የግሎባል ፈንድ አፈጻጸም ሁኔታ ላይ የሚወያይ መደበኛ ስብሰባ በኔፕ ፕላስ
አስተናጋጅንት በ ኔፕ ፕላስ ጸ/ቤት አደራሽ ተካህዷል፡፡ በዚህ ለግማሽ ቀን
በተካጌደው ውይይት ላይ የሀገር ውስጥ ያሉ የግሎባል ፈንድ ቡድን አባላት
(Global Fund Country Team) ና የሲቪል ማህበረሰብ የሲሲኤም ኃላፋችና
አባላት፤ እንድሁም የኔፕ ፕላስ የማኑጅመንት ኮሚቴ አባላት ጨምሮ ከ30
በላይ እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን የግሎባል ፈንድ 7ኛ ዙር ( GC 7) ያለበት
ሁኔታ ለተሰብሳቢዎቹu ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

ፈንዱ ያለበት ሁኔታ በዶ/ር ግርማቸው ማሞ የሲሲኤም ኢትዮጵያ ምክትል
ሰብሳቢ የቀረበ ሲሆን እሳቸውም በርፖርታቸው በግሎባል ፈንድ የአሰራር ሂደት
ውስጥ የሲቪል ማህበረሰቡ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸሻለና የመወሰን
አቅማቸው በአሁኑ ወቅትም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር ግርማቸው ሪፖርታቸውን በመቀጠል የግሎባል ፈምድ ግራንቱ ለኤችአይቪ
መከላከልና መቆጣተር ሥራ፤ ለወባ መከላከያና ለቲቢ በመባል በሶስት
እንደሚከፈል አብራርተው በአሁኑ ወቅት በአፈጸጸም ደረጃቸው ለኤች አይቪ
መከላከያ የተመደበው ግራንት ከፈጻሚ አካላት ጋር ስምምነት ተፈርመው ወደ
ሥራ የተገባ ሲሆን ለቲቢና ለወባ መከላከያ የተመደቡት በጀት ግን ገና በህደት
ላይ ይገኛል ብሏል፡


ከሪፖርቱ በመቀጠል ስብሰበው ለውይይት ክፍት የሆነ ሲሆን በርካታ ጥያቄዎች
ከቤቱ ተነስተዋል፡፡ ከተሰብሳቢዎች ከተነሱትና የተሳታፊውን ትኩረት ከሳቡት
ጥያቄዎች መካከል በሚኒዛሪ ለውጥ ምክንያት የበጀት ዕቅድ ክለሳ ሲደረግ
የግልጽነት መጓደል፤ የተመደበው በጀት ለአአስተዳደራዊ ወጪና ለክትትልና
ምዘና ትኩረት አለመስጠትና በቂ በጀት አለመያዝ፤ ከአዲሱ የአሜሪካ ፕረዝዳን
ውሳኔዎች ጋር ተያይዘው የፕሮጀክቱ ቀጣይነት ስጋት በፈጻሚዎች ዘንድ
መከሰት፤ ወ.ዘ፣ቴ…የሚሉት ከቤቱ ቀርበዋል ፡፡
ከተሰብሳቢዎቹ ለተነሱት ጥቄዎች መልስ የሰጡት ሚሰተር ጆረጅ የግሎባል
ፈንድ ቡድን መሪ ሲሆኑ በመልሳቸውም የተከለሰው በጀት እንዳልጠደቀ ገልጸው
የገንዘቡ ዋና ተቀባይ የሆነው የጤና ሚነስቴር በተገኘበት በመጪው የካቲት ወር
ውስጥ የጋራ ስብሰባ እንደሚያሰናዱና እስከዚያውም ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር እንደሚመክሩበት ቃል በመግባት እስከዚያው ድረስ የበጀቱ መፈጸሚያ
ወቂት እየሄደ ስለሆነ ፕሮጀክቱን በመፈጸሙ ረገድ እንዲበረቱ አደራ ብሏል፡