ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) የግሎባል ፈንድን አፈጻጸም
ገመገመ
ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) የሩብ አመት የግሎባል ፈንድ ፕሮግራም
ግምገማ አካሄደ፡፡ ግምገማው ከሰኔ 8 እስከ 10 ቀን፣ 2015 ዓ.ም በአዳማ ናፊሌት ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በግምገማ መርኃ ግብሩ
ላይም የኔፕፕላስ ስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ የክልል ጥመረት ስራ አስኪያጆችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም የጤና
ሚኒስቴር ተወካዮች እና የኔፕፕላስ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
በኔፕላስ ክትትልና ምዘና መምሪያ ኃላፊ አቶ በላይ ረታ ፕሮገራሙን ካስተዋወቁ በኃላ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት
የኔፕፕላስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ፕሮግራሙ ክልሎች በምን ሁኔታ ላይ
እንደሚገኙ ለመገምገም እና ለሚቀጥለው የግሎባል ፈንድ በጀት ጥያቄ ላይ ለመወያየት ፤ ልምድ ለመለዋወጥ እና የጋራ
እርምጃ ለመውሰድ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ካሳሁን ታደሰ የኔፕ ፕላስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ም/ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ ባላቆ በበኩላቸው ኤች አይ ቪ በአሁኑ
ወቅት ድምጹን አጥፍቶ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ በመሆኑ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡ የኤ አይ ቪ ስርጭትን
ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና የሚጫወተው ኔፕ ፕላስ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ጉሻ፤ በዚህ ረገድ
ድርጅቱ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ክልላቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይም ሁሉም የክልል ጥምረቶች የየሩብ አመት የፕሮግራም አፈጻጸማቸውን ሪፖርት አቅርበው ሰፊ
ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ክልሎች ያቀረቧቸው ሪፖርቶች በአብዛኛው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሲሆን፤ እንደ የክልሎቹ
ተጨባጭ ሁኔታም በስራቸው ላይ ገጥመዋቸው የነበሩ ተግዳሮቶችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ጥምረት ባቀረበው የሩብ አመት የፕሮግራም ሪፖርት በተጠቀሰው ጊዜ ያከናወናቸውን ስራዎች በዝርዝር
ያቀረበ ሲሆን እንደ መልካም ተሞክሮ ያነሷቸውን ነጥቦችም አስቀምጠዋል፡፡ ጥምረቱ በአብዛኛው በበጎ ፈቃደኞት የሚሰራ
እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ዋና የትኩረት አቅጣጫውም ቫይረሱ ኖሮባቸው ከክትትል የጠፉ ግለሰቦችን የማፈላለግ እና2
በመድሃኒት ላይ እንዲቆዩ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እነዚህን ተግባራት በሚያከናውኑበት ወቅትም በርካታ ቫይረሱ
ያባቸው ወገኖች ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ መድሃኒታቸውን አቋርጠው ወደ ጸበል እና ገዳም መሄድ ፤ የጋራ እቅድ ሥራውን
በተመለከተ አለማቀድ ፤ ጥራት ያለው ሪፖርት በወቅቱ አለማቅረብ፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን አለመስጠት፤ የሰራተኞች
መቀያየር እና የጸጥታ ችግር ዋና ዋናዎቹ በአፈጻጻም ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው ተብለዋል፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶችም
በተለያየ መልኩ መቋቋም መቻላቻው በሪፖርቱ ወቅት ቀርቧል፡፡
ጥምረቱም የራሱ የሆኑ ምርጥ ተሞከሮ ያላቸውን ያቀረበ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም ከለጋሾች ከሚለቀቅላቸው ፈንድ
በተጨማሪ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጽፈው ሃብት ማፈላለግ መቻላቸው፤ በአፍላ ወጣቶች ላይ የኤች አይ ቪ መከላከል
ስራዎችን መስራታቸው፤ ማጭበርበር እንዳይከሰት የሚያግዝ ፖሊሲ ማውጣታቸው እንዲሁም አደጋ የማስወገጃ
መንገዶችን ስራ ላይ ማዋል ናቸው ተብሎዋል፡፡
የስብሳባው ተሳታፊዎች በከፊል
ሌላው በጉባኤው ላይ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረበው የሱማሌ ክልል ጥምረት ነው፡፡ ጥምረቱ ልክ እንደሌሎች ጥምረቶች
ሁሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት በዝርዘር ያቀረበ ሲሆን፤ በዋናነትም አድቮኬሲ ስራዎች ላይ ትረት
አድር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በዚህ በተቀመጠው ጊዜ ውስት 46 ከህክምናው ወጥተው የነበሩ ታካሚዎችን
ወደ ህክምና መመለስ መቻሉን ገልጿል፡፡ ጥምረቱ እነዚህን ስራዎች በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ ሆኖ እያከናወነ
እንደሆነ የገለጸ ሲሆን፤ በበጀት እጥረት ምክንያት ስራውን እየሰራ ያለው በአንድ ከተማ ላይ ብቻ እንደሆነም አንስቷል፡፡
በተጨማሪም ሶስት ማህበራት ቢሮ እንደሌላቸው ተገልጿል፡፡ ከቤቱ በተሰጠው ምላሽም ጥምረቱ የአድቮኬሲ ስራ የሚሰሩ
ሰዎች ራሰቸውን ግልጽ አድርገው እንዲያስተምሩ ቢደረግ መልካም ነው፤ ኔፕፕላስን ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ ከክልሉ ጤና ቢሮ
ጋር በጋራ በመስራት የቢሮ እና የመሳሰሉ ችግሮቹን ለመቅረፍ ቢሰራ የሚል ሃሳብም ተሰጥቷል፡፡
በመቀጠል የአማራ እና የጋመቤላ ጥምረቶች የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ የአማራ ጥምረትም በሪፖርቱ
ምንም እንኳን ክልሉ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የቆየ ቢሆንም በተቻለው አቅም ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች ተገቢውን
አገልግሎት በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ጥምረቱ የራሱን ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ገልጿል፡፡ በቀጣይም የበለጠ ስራ ለመስራት
የልምድ ልውውጥ ማድረግ ያስፈላጋል፤ በዚህም ድክመቶቻችንን ለማስወገድ እና ጥንካሬያችንን ለማስቀጠል ይረዳናል
ብለዋል፡፡ የጋመቤላ ጥምረት በበኩሉ በዋናነት ታካሚዎችን ወደ ህክምና የመመለስ ስራዎች ላይ አተኩሮ እየሰራ መሆኑን
የገለጸ ሲሆን ተጨማሪ ፋሲሊቲዎችን በመክፈት የጠፉትን ሙሉ በሙሉ መመለስ መቻሉን በሪፖርቱ አስቀምጧል፡፡3
በተጨማሪም ከግሎባል ፈንድ ድጋፍ ውጪ ጥምረቱ የራሱን ገቢ በመፍጠር እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካላት የምግብ
ድጋፍ እያደረገ መሆኑን እንደ ጥሩ ተሞክሮ አስቀምጧል፡፡ ሰፖርቲቭ ሱፐርቪዢን በመዳከሙ የተነሳም ዶክመንቶች
በአግባቡ ተደራጅተው የመያዝ ችግር እንዳለ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በቀጣይነት ሪፖርቱን ያቀረበው የአዲስ አበባ ጥምረት በበኩሉ ከተማዋ የኤች አይ ቪ ስርጭት ከፍተኛ የሆነባት ከተማ
እንደመሆኗ የሚፈለገውን ያህል መስራት እንዳልተቻለ ገልጿል ፡፡ በከተማዋ ውስጥ 58 ያህል ከፍተኛ ኤች አይ ቪ ስርችት
ስጋት ያለባቸው ወረዳዎች ያሉ ቢሆንም ጥምረቱ እየሰራ ያለው ከ3ቱ ወረዳዎች ጋር ብቻ መሆኑንም እንደማስረጃ
አስቀምጧል፡፡
በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የነበረችው ትግራይ ክልል ጥምረትም የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን፤ በክልሉ ላይ
በጦርነቱ ሳቢያ ብዙ ነገሮች በመውደማቸው ቫይረሱ ያለባቸው ወገኖች ደግሞ የበለጠ ተጎጂዎች ሆነዋል፡፡ በሪፖርቱ
እንደተገለጸው የቫይራል ሎደ መለኪያ፤ የመመርመሪያ መሳሪያዎች፤ የኮንዶም እና የመድሃኒት እጥረት ከመኖሩም በላይ
መድሃኒቱን ያገኙ ሰዎች እንኳን መድሃኒቱን ለመዋጥ የሚያስፈልጋቸው ምግብ እየተቸገሩ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅም ቢሆን
ሌሎች የሚወስዱትን መድሃኒት ማግኘት ስለማይቸሉ ከአመታት በፊት ይሰጥ የነበረውን ጸረ -ኤች አይ ቪ መድሃኒት
በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ እና ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞችንም ለመታከም ችግር ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተብራርቷል ፡፡
የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ካለፈ ከስድስት ወር በላይ በመሆናቸው መሳሪያዎች ጭምር በመጠቀም ላይ እንደሆኑ ሪፖርቱ
ገልጿል፡፡ ይህ ደግሞ ትክክለኛውን ውጤት ማሳየት ስለማይችል ነገሮችን የበለጠ ውስብስብ እያደረጋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
በርካታ ህጻናት ከቫይረሱ ጋር እየተወለዱ እንደሆነና እንዲሁም ችግሩ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ስራቸውን ለመስራት ትልቅ
እንቅፋት እንደፈጠረባቸውም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
የሃረሪ፤ የድሬደዋ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ክልል ጥምረቶችም የየራሳቸውን የእፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤
ሁሉም ክልሎች የየራሳቸውን ተግባራት በዝርዘር አቅርበዋል፡፡ በቤኒሻነጉል ጉሙዝ ጥምረት የበለጠ ትኩረት ሰጥቶት
የሚሰራው በጎ ፈቃደኞችን በማበረታታት መሆኑን ሪፖርቱ ያመላከተ ሲሆን፤ በተጨማሪም በሰውነት ውስጥ ያለውን
የቫይረስ መጠን ወደማይታይ መጠን ማውረድ ዋናው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የለው ጉዳይ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ ሆኖም
ግን እነዚህን ተግባራት በሚፈለገው መጠን እንዳያከናውን የባለሞያ እጥረት እንዳለበት ጥመረቱ ገልጿል፡፡
ሁሉም ጥምረቶች ስራዎቻቸውን በሚሰሩበት ወቅት ያጋጠሟችን ተግዳሮቶች ያስቀመጡ ሲሆን፤ዋና ዋናዎቹም የተቀናጀ
እቅድ አለመኖር፤ጥራት ያለው ሪፖርት አለመቅረብ፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አለመኖር እና የባለሞያ እጥረት እንዲሁም
የበጀት እጥረት እና አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጸጥታ ችግሮች ናቸው፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋምም የየራሳቸውን
እርምጃዎች እንደወሰዱ ጥምረቶቹ ገልጸዋል፡፡
ጥምረቶቹ የስራ አፈጻጸም ሪፖርቶቻቸውን ማቅረባቸውን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምለሽና
ማበራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ለጥያቄዎቹና አስተያየቶቹ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት አቶ ካሳሁን ፤ በቀጣይ ሁሉንም ያሳተፈ
እቅድ እንደሚታቀድ እንዲሁም ሁሉም ጥምረቶች ተገናኝተው በመወያየት ወደ ፍጻሜ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ስልጠናን
በተመለከተ ሁሉም ጥምረቶች ለኬዝ ማናጀሮችና አድሄራንስ ሰፖረተሮች እንደሚሰጥ እንዲሁም የባለሞያ ስልጠናም
እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ ከህክምና የጠፉትን ወደ ህክምና መመለስን በተመለከተ ክፍያው ለአምጪው አሰራሩ በካስኬድ
እየታየ ፈላጊው ያደረገው ጥረት አና የሄደባቸው ሂደቶች በሚያቀርበው ሪፖርት በደንብ ተገምግመው መሆን አለበት
ብለዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሊ እና አፋር ክልሎች ትኩርት የሚፈልጉ ክልሎች ቢሆኑም እገዛ እንዳልተደረገላቸው
የገለጹት አቶ ካሳሁን፤ በቀጣይ ግን ማህበራትንም ጭምር ያሉበትን ሁኔታ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የመቃኘት እቅድ
እንዳለም አብራርተዋል፡፡ በአቅም ግንባታ ደረጃም በትብብር እንሰራለን ብለዋል አቶ ካሳሁን፡፡ በቫይረሱ የሚያዙ ሴቶች
ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ድርጅቱ ወደፊት ከሴቶች ጥምረት ጋር በመሆኑ ሁሉም ጥመረቶች ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባም
አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት አቶ ካሳሁን ኔፕፕላስም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
አቶ ካሳሁን ታደሰ እና አቶ በላይ ረታ ውይይቱን ሲ መ ሩ
በቀጣይ ከጤና ሚኒስቴር ከመጡ ተወካዮች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ለተወካዮቹ ከኔፕፕላስ የተወከሉ አባላት
የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ላይ የማህበራት ቁጥር ቢጨመር፤
ለአደሄረንስ ሰፖርተሮችና ኬዝማናጀሮች የቁሳቁስ ዝግጅት ቢደረግ፤ለሰፖርቲቭ ሱፐርቪዠን በጀት ቢመደብ፤ህክምና
ያቋረጡትን በተመለከተ በርካታ ድርጅቶች ስለሚነቀሳቀሱ ድግግሞሽ አና የሃብት ብክነት እየተፈጠረ ስለሆነ ፈቃድ አስጣጡ
ቢፈተሽ፤ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት ቢሰጥ እና በጀት ከመንግስት የሚያገኙበት ሁኔታ ቢመቻች፤ የሚሉት ናቸው፡፡ የጤና
ሚኒስቴር ተወካዮችም የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የመጀመሪያው ምላሽ ሰጪ አቶ ሃብታሙ ካሳ በፌደራል ኤች አይ ኢ መከላከል እና መቆጣጠር ጽ/ት ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ
ዴሽክ ኃላፊ ሲሆኑ በምላሻቻም የጋራ እቅድን በተመለከተ ምንም አይነት አቅዶችም ሆኑ ሃገራዊ ዳሰሳዎች ሲዘጋጁ በጋራ
ነው፡፡ የተሰሩ ስራዎችም መገምግ ያለባቸው በጥምረት መሆን አለበት፡፡ ኔፕፕላስ የግሎባል ፈንድን በጀት ያውድድር
ለመውሰድ በመጀመሪያ ደረጃ ያንን መስራት የሚችል ቁመና ያለው ድርጅት መሆን ያስፈልጋል፡፡ ይሄንን እድል ለማግኘት
የመከላከል ስራ ላይ ትኩረት ያደረገ ተቋም ይኑራችሁ፡፡ ስራቸሁን በሚፈለገው መልኩ መስራት ከቻላቸሁ እና ካሳመናችሁ
እዚህ ደረጃ ላይ የማትደርሱበት ምክንያት የለም፡፡ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በመርዳት ረገድ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር
ይኖርባችኋል፡፡ ቫይረሱ ያለባቸው ዜጎች ዩኒቨርሲቲ ሲመደቡ እዚያወ ባሉበት አካባባ እንዲመደቡ በማገዝ እንዲሁም ፤
ሰርተው መለወጥ ለሚፈልጉ ገንዘብ ከሚያበድሩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቀላሉ ብድር አግኝተው ራሳቸውን እንዲጨሉ
በማድረግ በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባችኋል፡፡
ኔፕፕላስ በምክር ቤት ውክልና ማግኘት ከቻለ በርክት ተጽኖ ፈጣሪ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ የማድረግ አቅም ይኖረዋል፡፡ ቦታው
በመንግስት ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ለመፍጠር ስሚረዳ በዚህ ላይም በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠይቃል፡፡ የሃገር ውስጥ
በጀት ላይ ማተኮር የሚለው የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ የውጪ እርዳትዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ስለሚመጡ የሃገር
ውስጥ የሃብት ምንጮች ላይ ትኩረት ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ተሰብሳ ቢ ዎ ች በከፊል
አቶ ሐየሎም አሰፋ የCCM ኢትዮጵያ ተወካይ በሰጡት ምላሽ ኔፕ ፕላስ ከመንግስት በጀት እንዲበጀትለት የማድረጉ ስራ
ብሄራዊ ስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ እንዲካትት በእቅድ ወቅት ይሰራል፡፡ ግጭት በሚፈጥርበት ወቅት ቫይረሱ ያለባቸው
ወገኖች ይበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ የተነሳውም የአቅዱ አንድ አካል እንዲሆን ጥረት ይደረጋል፡፡ ቀላል ስራ ስለማይሆን
ነገሮችን ማስተካከል እና መታገል ያስፈልጋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ጽ/ቤት መሪ ስራ አስጻሚ የሆኑት አቶ ፈቃዱ ያደታ በሰጡት
ማብራሪያም መዋቅሮች ሲቀያየሩ ነገሮችን በነበሩነት ማስኬድ ይከብዳል፡፡ የክልል አመራሮች እዚህ ጋር የሚነሱትን
ጥያቄዎች በጥልቀት ልትመረምሩ እና አቅጣጫዎቹን ወደ ተግባር ልትቀይሩ ይገባል፡፡ ዝም ብሎ መስራት ብቻ ሳይሆን
ጊዜው የሚፈልገውን ስራ መስራት እና በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ይጠይቃል፡፡ ከየቤተሰቡ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ሰዎችን
ከያዝን ስርጭቱን በቀላሉ መቆጣጠር እንችላለን፡፡ ከተለመደው አስራር ወጣ ብሎ በመግባባት፣ አቅምን አሟጦ በመጠቀም
ነው ለውጥ ሊመጣ የሚቸለው፡፡ ኔፕፕላስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለ ኤች አይ ቪ መቆጣጠር እና መከላከል
የሚመደበውን የግሎባል ፈንድ በጀት መጠቀም አለበት፡፡ ይሄንን እድል ለመጠቀም ድርጅቱ ራሱ በሚፈለገው መልኩ
ማስተካከል እና ስራዎቹን በሚገባ ማከናወን ይኖርበታል፡፡ የቀድሞ እቅዶቻችሁን እንዳትደግሙ፡፡ የወጣቶችን ተጋላጭነት
በተመለከተ አሁን ላይ ያለው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ነው፡፡ ቀድሞ ዋና ዋና ተጠቂ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አሁን ላይ ብዙ
ናቸው፡፡ ሴቶችን ከገጠር ወደ ከተማ የሚያመላልሱ ሰዎች፤ ከቤት እንኳን ወጥተው የማያውቁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና
አፍላ ወጣቶች በጣም ተጋላጭ እየሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ስለ ኤች አይቪ የማያውቁ ናቸው፡፡ በቀጣይም እንደየ ክልሎቹ
ተጨባጭ ሁኔታ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መድረስ ያስፈልጋል፡፡ አዲስ የመያዝ ምጣኔ አሁንም
ያልቀነሰው ከ15 እስከ 24 አመት ባሉት ላይ ነው፡፡ በት/ት ሚኒስቴር ውስጥ እንኳን ቀድሞ በተለያዩ ክበባት ይደረግ የነበረው
እንቅስቃሴ አሁን ላይ የለም፡፡ ይሄ ተመልሶ እንዲጀመር ተፅኖ ማሳደር አለባቸሁ፡፡ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክት እንዲመጡ
ማድረግ እና ሃገር ውስጥ ሃብት ላይ በማተኮር በግጭት ወቅት መጠቀም ያለባችሁ ሜካኒዝም ላይ አስቀድማቸሁ ስሩ፡፡
አቶ ሃብታሙ ካሳ ፈቃ ዱ ያደታ እና አቶ ሃየሎም አሰፋ ተሰብሳቢዎችን ሲያወያዩ
ቫይረሱ ያለባቸው ወጣቶች የስነልቦናና ማህበራዊ ስልጠና ላይ አተኩራችሁ ልትሰሩ ይገባል፡፡ ወደ ግንኙነት ሲገቡ መቋቋም
የሚችሉበት ሁኔታ ላይ አቅዳችሁ ከሰራችሁ እኛም እናግዛችኋለን፡፡ አማራ ክልል ያለው ችግር ተደራራቢ ቢሆንም በአዲስ
አበባ ዙሪያም የባሰ ችግር አለ፡፡ በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፡፡ የመድሃኒት እጥረት እንዳይኖር
ጥናትን መሰረት ያደረገ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ የመጀመሪያው 95 በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የመናውቀውም በጥናት ነው፡፡
የግብኣት ችግሮች ስላሉ የችግሩን መነሻ በማጥናት ላይ ነን ፡፡ መድሃኒት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሚላክበት ሁኔታ ላይ
አብረን እንሰራለን፡፡ ክልሎች ሪቪው ሚቲንግ ሲያካሂዱ የጤና ሚኒስቴር ሃላፊዎች፤ የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና
ዳይሬክተሮች በተገኙበት መሆን አለበት፡፡ በዚያ መድረክ ላይ በሚገባ ተወያይቶ የተሻለ ስራ መስራት ይቻላል በማለት
ድርጅቱ ሊያግዙ የሚቸሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡