በኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎረክስ ኦፍ ኤች አይቪ ፖሲቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) እየተተገበረ ያለውና
በጸረኤች አይቪ ህክምናና ቁርኝት ላይ ያተኮረው ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው በአዳማ ከተማ ናፍሌት ሆቴል ከነሓሴ 3 አስከ 6 2015 ዓ.ም በተካሄደው የዕቅድ
ክለሳ አውደ ጥናት ላይ ሲሆን፤ በአውደ ጥናቱም ላይ የየክልሉ የቦርድ ተወካዮች፤ ዳይሬክተሮች፤
የፕሮግራም ኃላፊዎች ከ12ቱም ጥምረቶች የተወጣጡ ከ67 በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች ተሳታፊ
ዎች እንዱሁም የጤና ሚኒስቴር ተወካዮችም እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡


የዕቅዱ ተሳታፊዎች በከፊል
በዚህ በአቶ ካሳሁን ታደሰ የድርጅቱ ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችወሁ ንግግር በተከፈተው አና
በድርጅቱ የቦርድ ፕሬዝዳንት በአቶ አብዱራሂማን ከማል መልዕክት በተዘጋው ስብሰባ ላይ
እንደተብራራው ባለፉት 1 ዓመት ከ6 ወራት ብቻ በቤት ለቤት እንክብካቤ አገልግሎት 131 ሺህ 734
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች ህክምናቸውን እንዳያቋርጡ የምክክር አገልግሎት
አግኝተዋል፡፡ በሪፖርቱ ከ,14 ሺህ725 በላይ የሚሆኑት ከህክምናቸው ጠፍተው የነበሩ ታካሚዎች
ደግሞ አስፈላጊው ፍለጋና የምክክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ወደ ህክምናቸው እንዲመለሱ
እንደተደረጉ ተግልጿል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከ 28 ሺህ 499 በላይ የሚሆኑና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ለተለያዩ
ድጋፎች ወደ ተለያዩ ድርጅቶች ተልከው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ እንደተደረገ ከቀረቡት
ሪፖርቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡ አድሎና ማግለልን ለመቀነስም ከ33 ሺህ 555 በላይ የህብረተሰብ
ክፍሎች የግንዛቤ ማዳበሪያ ትምህርት ተሰጥቶቿል ተብሏል፡፡

ተሳታፊዎች በከፊል
በአፈጻጻሙ ወቅት የገጠሟቸውን ችግሮች እያንዳንዱ ክልል ተራ በተራ ያቀረቡ ሲሆን፤ የፍላጎትና
አቅርቦት አለመጣጣም፤ የዕቅዱ ከላይ ተዘጋጅቶ መውረድና በአፈጻጻሙ ላይ ግልጽ አቅጣጫ
አለመቀመጥ፤ የሪፖርት ቅጾች ግልጽነት መጓደልና የመሳሠሉት ናቸው ተብሏል፡፡ በተነሱት ችግሮች
ዙሪያም ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን፤ በመቀጠልም የሚቀጥለው የ2016 የአንድ አመት ዕቅድ
ቡድን በቡድን በመከፋፈል ከልሷል፡፡
ኔፕ ፕላስ እስከ ፕሮጀክቱ መጨረሻ ድረስ 300 ሺህ ለሚሆኑት ተጠቃሚዎች የጸረኤችአይቪ
ህክምናቸውን እንዳያቋርጡ ለመደገፍ የ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የ3 ዓመት ፕሮጀክት ከጤና
ሚንስቴር ጋር መፈራረሙ ይታወሳል፡፡