ኔፕ ፕላስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት አካሄደ ኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) 16ኛ መደበኛ
ጠቅላላ ጉባኤውን በባህርዳር ከተማ ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው ሲሆኑ በንግግራቸው ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሶስት 90ዎች ፕሮግራም ወደ ሶስት 95ቶች መለወጡን አስታውሰው በተለይ በአሁኑ ሰኣት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን 95 ለማሳካት ሰፊ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት ይህ ታላቅ ጉባኤ መካሄዱ ለፕሮግራሙ መሳካት ሰፊ አበርክቶ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ታሪኩ በላቸው የአማራ ክልል ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አያይዘውም ዓለምን እየፈተነ ያለው የኮቪድ 19 ወረርሽን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዘመቻ አስቸጋሪ እንዲሆን እያደረገው ካሉ በኋላ በኢኮኖሚ ጠንካራ ያልሆኑና አንስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ሴቶች እህቶቻችን የኮሮና ወረርሽኝ ኑሯቸውን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል፡፡
በተለይ ይህ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት እንዲጨምር በማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ እንዳለም የሚያመለክቱ መረጃዎች እንዳሉ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ምክትል ቢሮ ኃላፊው በንግግራቸው መጨረሻም ጉባኤው በእቅዶቻቸው ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመከላከል ስራን እንዲካትቱ ጥሪ አድርገው የአማራ ክልል መንግስት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመከላከል ረገድ ለሚደረጉ ጥረቶች አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ድጋፍ ለመስጠት ከክልሉም ሆነ ከብሄራዊ ጥምረቱ ጎን እንደሚቆም ቃል በመግባት ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን አገባደዋል፡፡ ከመክፈቻው ንግግር ቀደም ብሎ የኔፕ ፕላስ ዋና ስራ አስኪጅ ለተሰብሳቢዎቹ ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ኔፕ ፕላ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት በርካታ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በንግግራቸውም ኔፕ ፕላስ ከሲዲሲ እና ከግሎባል ፈንድ ውጪ ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብና የአይነት እንደዚሁም የቴክኒክ ድጋፎች ማገነቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ ለደርጅቱ ችግር ሆኖ የመጣው መላው አለምን ፈታኝ የሆነው የኮቪድ 19 ክስተት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አቶ መኮንን አለሙ የኔፕ ፕላስ ዋና ዳይሬክተር ለጉባኤተኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ሲያደርጉ ይህንኑ ወረርሽኝ ለመከላከልም ኔፕ ፕላስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ የእጅ ማጽጃና የፊት መሸፈኛ ማስኮችን በድጋፍ መልክ ማግኙቱን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እድላም ገ/ስላሴ በበኩላቸው ቦርዱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መደበኛ እና አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማካሄድ የኔፕ ፕላስ የስራ ግምገማ በማድረግ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ አቅጣጫዎችና የቅርብ ድጋፍ ሲያደርግለት መቆየቱን አስታውሰው ከዚህ ውጭ በአንዳንድ የክልል ጥምረቶች ላይ በታዩ ችግሮች ላይ በቦታው ድረስ በመገኘት የመፍትሄ ሀሳቦችን ተሰጥተዋል ብለዋል፡፡ አቶ እድላም ገ/ሥላሴ የኔፕ ፕላስ ቦርድ ሰብሳቢ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በሶስት ቀናት ቆይታቸው የድርጅቱን የቦርድ ሪፖርትና እቅድ፣ የጽቤቱን ሪፖርትና እቅድ፣ የኦዲት ሪፖርት እና አዲሱን የመተዳደሪያ ደንብ አጽድቋል፡፡