ኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን
ግንቦት 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊሳክ ሆቴል አካሄደ፡፡ በጉባዔው ላይም የድርጅቱ የቦርድ አባላት፡
የጠቅላላ ጉባዔ አባላት፣ የኔፕፕላስ ሰራተኞች እና አጋር ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡
በጠቅላላ ጉባዔው ላይ በርካታ መልዕክቶች፣ የየስራ ክፍሉ የስራ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲሁም የ2023 አመታዊ
እቅድ የቀረቡ ሲሆን ከጉባዔው ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች እንዲሁም ጥቆማዎች የተሰነዘሩ
ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ በሚመለከተው አካላት ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በጉባኤው ላይ በመጀመሪያ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኔፕፕላስ እክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ
ካሳሁን ታደሰ ሲሆኑ፣ እርሳቸውም በንግግራቸው ድርጅቱ ከ20 አመታት በላይ ለችግር የተዳረጉ ወገኖችን
ከወደቁበት ችግር እያነሳ የቆየ ድርጅት ቢሆንም አሁን ግን በተለያዩ ምክንያቶች ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት
በመሄዱ ቀድሞ አብረው ይሰሩ የነበሩ አጋሮቻቸን ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው ብለዋል፡፡ አቶ ካሳሁን ድርጅቱን አሁን
ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው በመጠቆም፤ ደርጅቱን ወደ ቀድሞ አቋሙ
ለመመለስ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ አና ተስማመቶ በየደረጃው ያለበትን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም
አሳስበዋል፡፡

አቶ ካ ሳ ሁ ን ታደሰ የኔፕ ፕላስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር
በማስከተል በፌደራል ጤና ሚኒስቴር ኤች አይ ቪ መከላከል እና መቆጣጠር ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ዴስክ
ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ካሳ ከማንኛውም ጊዜ በላይ አንድ ሆነን ጥምረቱን መደገፍ አለብን ያሉ ሲሆን፤ ድርጅቱ
ለተቋቋመለት አላማ መኖሩን እየዘነጋ የመጣ ስለሆነ መንቃት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
ኔፕ ፕላስ ለጤና ሚኒስቴር የውጭ አካል ሳይሆን እንደ ራሳችን አንዱ ክፍል አድርገን የምቆጥረው ስለሆነ
ድክመቱን ማየት አያስደስተንም ብለዋል አቶ ሀብታሙ፡፡ ሶስቱን 95 በማሰካት ረገድ የኔፕ ፕላስ ሚና ከፍተኛ
እንደሆነ የገለጹት አቶ ሀብታሙ፤ አሁንም የቫይረሱን ስርጭት ወደ 0.3 በመቶ ለማውረድ እየተጫወተ ያለው
ሚናም ቀላል የሚባል ባለመሆኑ፤ የጤና ሚንስቴር አንዱ አካል ነው የምንለው በምክንያት ነው ብለዋል ኃላፊው፡፡
በአገራችን ብዙ ድርጅቶች ቢኖሩም ኔፕ ፕላስን የሚተካ ሊኖር አይችልም ያሉት አቶ ሀብታሙ፤ ጥምረቱ ከሌሎች
አጋር ድርጅቶች ጋር ቁርኝቱን የበለጠ አጠናክሮ ለመስራት ራሱን በከፍተኛ ደረጃ ምቹ ማድረግ እንዳለበትም
አሳስበዋል፡፡ ያሉትን የጤና ፖሊሲዎች መሬት ለማስያዝ እና ተግባራዊ ለማድረግ የኔፕ ፕላስም አስተዋጽኦ
ከፍተኛ እንደሆነ ነው አቶ ሃብታሙ የገለጹት፡፡ ሚኒስትሩ ወደፊትም ኔፕ ፕላስን በሁሉም መንገድ ለመደገፍ እና
ተጠያቂነትን ለማስፈን የጂፓ ፕሪንሲፕልን ለመተግበርም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ በድርጅቱ በኩል ግን
ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ በሰፊው አቅዶ መንቀሳቀስ ያለበት ተጽእኖ ፈጣሪ ድርጅት
ሆኖ መታየት ባለበት ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ሃብታሙ፤ ይሔን ማድረግ ከቻለ ከመንግሰት በጀት
ማስለቀቅም ሆነ ሌሎች ለጋሽ አካላትን ለመሳብ ቀላል ይሆንለታል፡ በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

አቶ ሃብታሙ ካሳ በፌደራል ጤና ሚኒስቴር ኤች አይ ቪ መከላከል እና መቆጣጠር ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ዴስክ ኃላፊ
በመቀጠል የኔፕፕላስ የበጀት አመቱ የስራ ክንውን ሪፖርት በድርጅቱ ክትትልና ምዘና መምሪያ ሃላፊው አቶ
በላይ ረታ የቀረበ ሲሆን፤ በሪፖርቱ የቀረቡት ዋናዋና ነጥቦችም የሚከተሉት ናቸው፡፡ እንደ ማኔጅመንት ከፍተኛ
ትኩረት ተሰጥቶ ከተሰራባቸው ስራዎች ዋና ዋናዎቹ የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት እና የፈረንሳይ ፕሮጀክቶችን
ለማስቀጠል ፤የሲዲሲ ፕሮጀክት ቁሳቁሶችና ተሸከርካሪዎች እንዳይወሰዱ፤ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወጣቶች
ማህበር (አስክ አስ) እንዲመሰረትና እንዲጠናከር ጥረት ማድረግ ተጠቃሽ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ የፍራንስ
ኢኒሸቲቭ ፕሮጀክት ከፈረንሳይና ከአገር ውጪ በመጡ ኦዲተሮች ኦዲት እንዲያደርጉ ተደርጓል ብሏል፡፡
በተጨማሪም በኤል ኢኒሸቲቭ በጀት ለአቻለአቻ አስተማሪዎችና ፕሮጀክት ኦፊሰሮች፤ ለአማካሪዎች እና በግሎባል
ፈንድም የአሰልጣኝ ስልጠና መሰጠቱን፤የጥምረቶችና የማህበራት መሪዎችም የአመራር ክህሎት ስልጠና
እነደተሰጠ አብራረተዋል አቶ በላይ በርፖርታቸው፡፡ ወርክ ሾፕን በተመለከተም በተለይ አድሎና ማገለልን
ለመቀነስ ከተለያዩ የፓላማ አባላት እና የሲቪል ሰርቪስ አባላት፤ከክልሎች እና የጉዳዩ ባለቤት ከሆኑ አካላት ጋር
በርካታ ስብሰባዎች ተካሂደዋል ተብሏል በሪፖርቱ፡፡ በድጋፍና እንክብካቤ ደግሞ 12,363 ከህክምና ቀጠሯቸው
የጠፉ ደንበኞች ፍለጋ ተደርጎላቸው ወደ ህክምና አገልግሎት የተመለሱ ሲሆን፤ 8,058 ድጋፍና ክብካቤ
የሚያስፈልጋቸው ደንበኞችንም ወደ ድጋፍ ሰጭ አካላት ተልከው ድጋፍና ክብካቤ እንዲያገኙ ተደርጓል በአቶ
በላይ ገለጸ መሠረት፡፡ ህክምና የሚያስፈልጋቸው 2,719 ሰዎች ደግሞ ወደ ተለያዩ ጤና ተቋማት በመላክ ህክምና
እንዲያገኙ መደረጉም በዚው ርፖርት ተብራረቷል፡፡

አቶ አብ ዱርሃማ ን ከማ ል የኔፕፕላስ ቦርድ ሰብ ሳቢ
ከህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ጋር በተያያዘም 3ቱን 95 ለማሳካት እንዲረዳ በሶስት ቋንቋዎች የአን አንደ ደቂቃ
የቲቪ እና የሬዲዮ መልክቶች ተዘጋጅተው መሰራጨታቸውን፡ በዩዩ ላይ ያተኮረ 8000 ብሮሸሮች ታትመው
መሰራጨታቸውን፤ የአድሎና ማግለል የመቀነሻ ስተራቴጂ መዘጋጀቱን፤ የአድሎና ማግለል የጥናት ውጤትም
1000 ኮፒ ታትሞ መሠራጨቱን አቶ በላይ በርፖርታቸው አብራርተዋል፡፡


ተ ሰብ ሳቢዎ ች በ ከ ፊል
የኔፕፕላስ ስራ አመራር በበኩሉ የበጀት አመቱን ክንውን ያቀረበ ሲሆን በዋናነት ለድርጅቱ አዲስ ስራ አስኪያጅ
የመሾም፤ የውጭ ኦዲተሮችን ቅጥር መከናወኑ፤ ሃብት የማሰባሰብ እንዲሁም ስብሰባዎችን ማካሄድ ዋናዋና
እቅዶቹ የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ እቅዶች መካከል ያሳኩአቸውን የቦርድ ሰብሳቢው አቶ አብዱርሃማን ከማል
በዝርዝር አቅረበዋል፡፡ ታቅደው ያልተሳኩትንም በቀጣይ ለማሳካት በእቅዳቸው ውስጥ ማካተታቸው በዚው ጊዜ
ተገልጿል፡፡ በመቀጠልም የ2023 አመታዊ እቅድ የቀረበ ሲሆን፤ በዚህ በጀት አመት ከተያዙ እቅዶች መካከልም
ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው የኔፕፕላስን ገጽታ እና መልካም ስም የመገንባት ሥራ፤ በቂ ሃብት ማበልጸግ
አንዲሁም ወጥነት ያለውና የተስተካከለ የፋይናነስ አስተዳደር ማስፈን ናቸው፡፡
በዋና ዳይርክተር ልዪ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩ ከታቀዱ ስራዎች መካከል ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች
በተለያዩ መድረኮች እና ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ለሌሎች ወገኖች ድምጽ እንዲሆኑ ጠቃሚ ልመዶችንና
የሃብት ማግኛ እድሎች መፍጠር፤ መረጃዎችን፣ መልእክቶችና ውሳኔዎችን ማስተለላፍ፤ በተቋሙ ስር ያሉ አባል
ደርጅቶችናየስራ ክፍሎች የድርጅቱን አላማ ሊያሳካ በሚያስችል መልኩ ሃብት እንዲያፈላልጉ፤ አሳታፊ በሆነ
መልኩ እንዲያቅዱ እና እንዲተገብሩ እገዛ እና ክትትል ማድረግ፤ ስራዎች ውጤት ተኮር እንዲሆኑ መደገፍ እና
አዳዲስ ተግባራትን ማከናወን ብሄራዊ ጥምረቱን፣ የአባል ጥምረቶችን እና ማህበራትን ተቀባይነት እና
ተወዳዳሪነት ማሳደግ ከመንግስት አካላት፤ ከለጋሽ ድርጅቶች፣ ከባለድርሻ አካለት ፣ ከማህበረሰቡ እና
ከሚዲያዎች ጋር ቀጣይነት ያለው መልካም ግንኘነት በመፍጠር የድርጅቱን ገጽታና የገቢ ምንጭ ማሳደግ፤
ድርጅቱን በአጠቃላይ ብቁ ተወዳዳሪና ተወዳጅ ማድረግ ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በፕሮግራም
የስራ ክፍል የታቀዱ እቅዶችም ቀርበዋል፡፡

የጠ ቅላላ ጉባዔ መሪዎች
ከእነዚህ ተግባራት መካከልም ለ47 ፒር ኢዱኬተሮችና ለ 8 ኦፊሰሮች እንዲሁም ለ 30 አማካሪዎች፣ ለ31
ወጣቶች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት፤ ደምበኛ ተኮር አገልግሎት የሚሰጡ 34 የጤና ባለሞያዎችን እንዲሁም
ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ 235 የወጣቶች ቤተሰቦችን ማሰልጠን ፤ የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ቦታዎች ላይ 4
ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወጣት ማህበራትን እንዲመሠረቱ ማገዝ፤ በግሎባል ፈንድ 300 ኮሙኒቲ ኬዝ
ማናጀሮችንና 600 ኮሙኒቲ አድሄረንስ ሰፖርተሮችን በመጠቀም 12 ሺህ ከህክምና ክትትል የጠፉ ደንበኞችን
ፈልጎ መመለስ፤ በግሎባል ፈንድ የ3 ቀን የሪፍሬሽመንት ስልጠና ለ 300 ኮሙኒቲ ኬዝ ማናጀሮች እና ለ 600
ኮሙኒቲ አድሄረን ሰፖርተሮች ስልጠና መስጠት በዋናነት የተያዙ እቅዶች ናቸው፡፡
በጉባዔው ላይ ከቀረቡት እቅዶች ሌላኛው ደግሞ በህዝብ ግንኙነትና ኮመሙኒኬሽን መምሪያ የታቀዱ እቅዶች
ናቸው፡፡ በዚህ የስራ ክፍል ሊሰሩ ከታቀዱ ስራዎች መካከል በኤች አይ ቪ ምክንያት የሚደርሱ መድሎ
መገለሎችን ማስወገድ የሚረዱ ውይይቶችን ከሃይማኖት አባቶች ፣ የህግ አስፈጻሚዎችና መገናኛ ብዙኃን
ባለሞያች ጋር ማካሄድ፤ አስተማሪ መልእክቶችን በ5 ቋንቋዎች በክልል ኤፍ ኤም ጣቢያዎች ማስተላለፍ ፣አመታዊ
ህትመቶችን አሳትሞ ማሰራጨት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤው በቀረቡት ርፖርቶችና
ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ አጽድቆታል፡፡