ኔፕ ፕላስ የአለም የኤድስ ቀንን በኮምበልቻ በሻማ ማብራት ስነሥርአት አስቦ ዋለ

የኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይቪ ፖዘቲቭዝ ኢን ኢትዮጵየ (ኔፕፕላስ) የቦርድ አባላት፤
የየክልል የስራ አስኪያጆች እንዲሁም የኔትዎረኩ ሰራተኞች የአለም ኤድስ ቀንን ሻማ በማብራት እና
ህይወታቸውን በቫይረሱ ላጡ ወገኖች ጸሎት በማድረግ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በኮምቦልቻ ልዑል
መኮንን ሆቴል አስበው ዋሉ፡፡
በእለቱ በነበረው የሻማ ማበራት ስነስርአት ላይም የኤድስ ቀንን ለማሰብ ቀይ ሪቫንን ማድረግ ትርጉም
እና ምንን እንደሚወክል በኔፕፕላስ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ጎንፋ ማብራሪያ
ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቀይ ሪቫን የሚደረገው በአራት ምክንያቶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንደ አቶ
ጌታቸው ገለጻ የመጀመሪያው ምክንያት የኤች አይቪ ጉዳይ ሁሉንም የሰው ልጅ ይመለከታል የሚል
ስሜት ለመፍጠር ሲሆን፤ በዚህም ሁሉም ሰው በያገባኛል ስሜት በመከላከሉ ስራ ላይ መሳተፍ
እንዳለበት ለማስገንዘብ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች ድጋፍና
እንክብካቤ እንደሚያስፈላጋቸው ለማመልከትና ለዚህም ሁሉም ከገጎናቸው መቆም እንዳለበት ለማሳሰብ
ነው፡፡ በሶስተኛነት የተቀመጠው ምክንያት ደግሞ ሌሎች ወገኖች በኤች አይ ቪ እንዳይያዙ መከላከል
በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ የመጨረሻው የቀይ ሪቫን ምልክትነት ቫይረሱ
በደማቸው ያለባቸውም ሆኑ የሌለባቸው ወገኖች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም
እጅ ለእጅ ተያይዞ መረባረብ እንዳለበት ለማስገንዘብ ነው ብለዋል በገለጻቸው፡፡
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከሻማ ማብራት ስነስርአቱ በመቀጠል እጅግ ጠቃሚ የሆነ
ውይይት ያደረጉ ሲሆነ፤ በውይይታቸው እንደጠቆሙትም የአለም ኤድስ ቀንን የምናስበው ምንም
እንኳን አኛ በህይወት ብንኖርም በቫይረሱ ምክንያት ከጎናችን ያጣናቸው በርካቶች በመሆናቸው እነሱን
በቁጭት በማሰብ እና በመዘከር ነው ብለዋል፡፡ እለቱን ስናስብም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን
ያጡ እና የተለዩንን ወገኖች በማሰብ እንዲሁም ቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው
ሁኔታዎችን በማመቻቸት መሆን አለበት ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡
ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው በተለይ ወጣቶች ከመድሃኒቱ ጋር ያላቸው ቁርኝት የላላ እንዲሁም
መሰላቸት እና መዘናጋት የሚታይባቸው ስለሆነ፤ እነዚህ ወጣቶች እኛ እዚህ ለመድረስ ያለፍንበትን
ፈታኝ መንገድ ተረድተው የራሳቸውን የተሻለ ህይወት መምራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ኔፕፕላስ አሁን ካለበት ወደ ተሻለ ሁኔታ ለመለወጥ እና ከፍ ለማድረግ ከሌሎች አካላት ጋር
ያለውን መስተጋብር ማስተካከል፤ እርስ በርስ መደጋገፍ እና መተሳሰብ እንዲሁም ጠንክሮ መስራትን
ይጠይቃል ያሉት ደግሞ አቶ አብዱራህማን ከማል የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ አቶ
አብዱራህማን በገለጻቸውም እርስ በርስ ተደጋግፈን ከሰራን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2030
ለመድረስ ያስቀመጠው ግብ ላይ ለመድረስ መንገዶች ይመቻቻሉ ሲሉም መተባበሩ ያለውን ጠቀሜታ
የሚያጎሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየተሰራ ያለው ሥራም ሆን
እየተሰጠ ያለው ትኩረት የተቀዛቀዘ ቢሆንም በተለይ ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ላለባቸው ወገኖች
ማሕበራት እየተሰጠ ያለው ተኩረት እጅግ በጣም አናሳ መሆኑም ተብራርቷል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት
ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ማሕበራትን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በምን መልኩ
ማስቀጠል ይቻላል የሚለውን ማጤን አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡ ለምሳሌ በደቡብ ክልል በአሁኑ ወቅት
ካሉ 43 ሺህ ቫይረሱ በደማቸው ካለባቸው ወገኖች መካከል 21 ሺህ የሚሆኑት በማህበር ያልታቀፉ
መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ በተለይ አድሄረንስ ሰፖርተሮችና ኬዝ ማናጀሮች ከጤና ማእከል ወደ ማህበር
ወርደው በመድሃኒት ቁርኝት ላይ እንዲሰሩ የአቅም ግንባታ ስራ ለማሰራት መንግስት ሃላፊነቱን
ቢውስድ መልካም ነው የሚሉ ምክረ ሃሳቦችም ተነስተዋል፡፡ በመጨረሻም በኔፕፕላስ ውስጥ ከዚህ
ቀደም በተለያየ የስራ ሃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ ነገር ግን በሞት የተለዩ ሰዎች ሊታወሱ
የሚችሉባቸው መንገዶች ማመቻቸት መልካም ነው በሚለው ሃሳብ ሁሉም ሰው በመስማማቱ የእነዚህን
ባለውለታዎች ፎቶግራፍና ህይወት ታሪክ በማሰባሰብ ለማስታወሻነት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ
ከስምምነት ላይ በመድረስ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

ኔፕ ፕላስ የአለም የኤድስ ቀንን በኮምበልቻ በሻማ ማብራት ስነሥርአት አስቦ ዋለ

የኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይቪ ፖዘቲቭዝ ኢን ኢትዮጵየ (ኔፕፕላስ) የቦርድ አባላት፤
የየክልል የስራ አስኪያጆች እንዲሁም የኔትዎረኩ ሰራተኞች የአለም ኤድስ ቀንን ሻማ በማብራት እና
ህይወታቸውን በቫይረሱ ላጡ ወገኖች ጸሎት በማድረግ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በኮምቦልቻ ልዑል
መኮንን ሆቴል አስበው ዋሉ፡፡በእለቱ በነበረው የሻማ ማበራት ስነስርአት ላይም የኤድስ ቀንን ለማሰብ ቀይ ሪቫንን ማድረግ ትርጉም
እና ምንን እንደሚወክል በኔፕፕላስ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ጎንፋ ማብራሪያ
ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቀይ ሪቫን የሚደረገው በአራት ምክንያቶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንደ አቶ
ጌታቸው ገለጻ የመጀመሪያው ምክንያት የኤች አይቪ ጉዳይ ሁሉንም የሰው ልጅ ይመለከታል የሚል
ስሜት ለመፍጠር ሲሆን፤ በዚህም ሁሉም ሰው በያገባኛል ስሜት በመከላከሉ ስራ ላይ መሳተፍ
እንዳለበት ለማስገንዘብ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች ድጋፍና
እንክብካቤ እንደሚያስፈላጋቸው ለማመልከትና ለዚህም ሁሉም ከገጎናቸው መቆም እንዳለበት ለማሳሰብ
ነው፡፡ በሶስተኛነት የተቀመጠው ምክንያት ደግሞ ሌሎች ወገኖች በኤች አይ ቪ እንዳይያዙ መከላከል
በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ የመጨረሻው የቀይ ሪቫን ምልክትነት ቫይረሱ
በደማቸው ያለባቸውም ሆኑ የሌለባቸው ወገኖች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም
እጅ ለእጅ ተያይዞ መረባረብ እንዳለበት ለማስገንዘብ ነው ብለዋል በገለጻቸው፡፡

 የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከሻማ ማብራት ስነስርአቱ በመቀጠል እጅግ ጠቃሚ የሆነ
ውይይት ያደረጉ ሲሆነ፤ በውይይታቸው እንደጠቆሙትም የአለም ኤድስ ቀንን የምናስበው ምንም
እንኳን አኛ በህይወት ብንኖርም በቫይረሱ ምክንያት ከጎናችን ያጣናቸው በርካቶች በመሆናቸው እነሱን
በቁጭት በማሰብ እና በመዘከር ነው ብለዋል፡፡ እለቱን ስናስብም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን
ያጡ እና የተለዩንን ወገኖች በማሰብ እንዲሁም ቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው
ሁኔታዎችን በማመቻቸት መሆን አለበት ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡
ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው በተለይ ወጣቶች ከመድሃኒቱ ጋር ያላቸው ቁርኝት የላላ እንዲሁም
መሰላቸት እና መዘናጋት የሚታይባቸው ስለሆነ፤ እነዚህ ወጣቶች እኛ እዚህ ለመድረስ ያለፍንበትን
ፈታኝ መንገድ ተረድተው የራሳቸውን የተሻለ ህይወት መምራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ኔፕፕላስ አሁን ካለበት ወደ ተሻለ ሁኔታ ለመለወጥ እና ከፍ ለማድረግ ከሌሎች አካላት ጋር
ያለውን መስተጋብር ማስተካከል፤ እርስ በርስ መደጋገፍ እና መተሳሰብ እንዲሁም ጠንክሮ መስራትን
ይጠይቃል ያሉት ደግሞ አቶ አብዱራህማን ከማል የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ አቶ
አብዱራህማን በገለጻቸውም እርስ በርስ ተደጋግፈን ከሰራን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2030
ለመድረስ ያስቀመጠው ግብ ላይ ለመድረስ መንገዶች ይመቻቻሉ ሲሉም መተባበሩ ያለውን ጠቀሜታ
የሚያጎሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየተሰራ ያለው ሥራም ሆን
እየተሰጠ ያለው ትኩረት የተቀዛቀዘ ቢሆንም በተለይ ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ላለባቸው ወገኖች
ማሕበራት እየተሰጠ ያለው ተኩረት እጅግ በጣም አናሳ መሆኑም ተብራርቷል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት
ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ማሕበራትን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በምን መልኩ
ማስቀጠል ይቻላል የሚለውን ማጤን አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡ ለምሳሌ በደቡብ ክልል በአሁኑ ወቅት
ካሉ 43 ሺህ ቫይረሱ በደማቸው ካለባቸው ወገኖች መካከል 21 ሺህ የሚሆኑት በማህበር ያልታቀፉ
መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ በተለይ አድሄረንስ ሰፖርተሮችና ኬዝ ማናጀሮች ከጤና ማእከል ወደ ማህበር
ወርደው በመድሃኒት ቁርኝት ላይ እንዲሰሩ የአቅም ግንባታ ስራ ለማሰራት መንግስት ሃላፊነቱን
ቢውስድ መልካም ነው የሚሉ ምክረ ሃሳቦችም ተነስተዋል፡፡ በመጨረሻም በኔፕፕላስ ውስጥ ከዚህ
ቀደም በተለያየ የስራ ሃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ ነገር ግን በሞት የተለዩ ሰዎች ሊታወሱ
የሚችሉባቸው መንገዶች ማመቻቸት መልካም ነው በሚለው ሃሳብ ሁሉም ሰው በመስማማቱ የእነዚህን
ባለውለታዎች ፎቶግራፍና ህይወት ታሪክ በማሰባሰብ ለማስታወሻነት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ
ከስምምነት ላይ በመድረስ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

About NEP

The NEP+, formerly known as AELWHA (Association of Ethiopians Living with HIV/AIDS), is established in October 2004 to raise and relay the collective voice of people living with HIV.

GPS Location of NEP+ Office

Contact Us

Address: Mexico Chamber of Commerce building 5th floor.
Phone: +251 111 659 1414/1818/1919
Fax: +251 111 659 1010
P.O.Box: 780 Code-1250
Email: eshetu@nepplus.org / aelwha@ethionet.et