የኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) 17ኛ
መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ግንቦት 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ከረዩ ሂል ሪዞርት
ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የኔፕ ፕላስ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ጫላ ባደረጉት ንግግር፤
ኔፕ ፕላስ ላለፉት 17 አመታት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት ከ200 ሺህ በላይ ቫይረሱ
በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በማህበር ተደራጅተው አድሎና መገለል እንዲቀንስና ለሀገራዊ
ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ፤
ማህበረሰቡም ራሱንና ቤተሰቡን ከወረርሽኝ እንዲጠብቅ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ራሳቸውን
ይፋ በማውጣት ትምህርት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ 2030 ሊደርስበት ያስቀመጠውን የ 95 ፤ 95 ፤ 95 እቅድ
ተግባራዊ ለማድረግ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ከጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ጋር
እንዲቆራኙ ወይም የህክምና ክትትላቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም መድሃኒቱን ጀምረው
ያቋረጡ ወገኖች በአፋጣኝ ወደ ህክምና ክትትል እንዲመለሱ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ
ይገኛል ብለዋል አቶ ባይሳ፡፡
የኔፕፕ ፕላስ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብድርሃማን ከማል በበኩላቸው፤ ለአዲሱ
የግሎባል ፈንድ ውድድር በቂ ዝግጅት በማድረግ ውጤታማ ሆኖ ለማሸነፍ መቻሉን
አብራርተዋል፡፡ ከአለፈው ጠቅላላ ጉባዔ ወዲህ ባለው ስራቸው ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን
ሰብሳቢው ሲገልጹም ፤ ወቅቱን ያልጠበቀ የሲዲሲ በጀት መቋረጥ፤ በርከት ያሉ ሰራተኞች
ስራቸውን መልቀቅ እና የበጀት እጥረት ዋናውናዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡ እነዚህን
ቸግሮችም በተለያየ መልኩ ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውን ሰብሳቢው ጨምረው
ገልጸዋል፡፡ የስራ አመራሮችን በተመለከተም የአመራርነት ሃላፊነታቸውን ያልተወጡትን
የብሄራዊ ጥምረቱ ስራ አስኪያጅ በአዲስ ተወካይ ቦርዱ መተካቱን ሰብሳቢው ጨምረው
ገልጸዋል፡፡
የበመቀጠል ጠቅላላ ጉባዔው የተጓደሉ እና ጊዜያቸውን የጨረሱ የጠቅላላ ጉባዔ
አመራሮች ምርጫ በህገ ደንቡ መሰረት አካሂዷል፡፡ ጉባዔው በሶስቱ አስመራጭ ኮሚቴ
አባላት አማካይነት አዲስ አመራሮችን የመረጠ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት አቶ ማሙሸ ንጉሴ
የጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢ ፤ወ/ሮ እቴነሽ እሸቴ የጠቅላላ ጉባዔ ም/ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ሙሴ
ማማጫ የጠ ቅላላ ጉባዔ ጸኃፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በተጨማሪም በድርጅቱ በቦርድ አባልነት ከሀረሪ ክልል፤ ከአዲስ አበባ እና ከሴቶች
ጥምረት የተወከሉትን 3 የክልል ተወካዮችን ጉባዔው በቦርድ አባልነት እንዲሰሩ ጉባዔው
ያጸደቀ ሲሆን፤ በተገጓደሉ ጠቅላላ ጉባዔ አባልነትም የጋመቤላ ክልል ወክሎ የላከው 1፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የላካቸው 2 እና ሴቶች ጥምረት የላካቸው 4 ተወካዮችን
አጽድቋል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔው በመቀጠልም በ2021 የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር የገመገመ ሲሆን፤
በመጀመሪያ የስራ አመራር ቦርዱን ሪፖርት በዝርዝር አይቷል፡፡
በቦርዱ ሪፖርት ላይ ከአባላት የተለያዩ ጥያቄናዎችና አስተያቶች የተነሱ ሲሆን፡
ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶችም የቦርዱ ሰብሳቢው ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ሰብሳቢው
በምላሻቸውም የተቋረጠውን የሲዲሲ ፕሮጀክት በተመለከተ ፕሮጀክቱን ለመመለስ ጥረት
እንደሚደረግ፤ የኔፕ ፕላስ በጀት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ በመሆኑ የድርጅቱ መመሪያዎችና
ደንቦችን በዚያ መልኩ እንደሚቃኝ አስረድተዋል ፡፡ የግሎባል ፈንድ አሰራሩ በአጠቃላይ
ስለተቀየረ የበጎ ፈቃደኞችን እና ሌሎች ሰራተኞችን አለማካተቱን የገለጹት ሰብሳቢው፤
በተጨማሪም በጦርነት የተጎዱ ክልሎችንና ሌሎች ድጋፍ የሚፈልጉ ማህበራትን ለመደገፍ
ቦርዱ ከ ጽ/ቤቱ ጋር የጋራ እቀድ አቅዶ እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ቦርዱ
ስራውን በአግባቡ እያከናወነ መሆኑን የተገነዘበ ሲሆን ፤ ለሚቀጥለው አመት የሃብት ማበልጸግ
ስራ እንዲሁም የውጪ የቦርድ አባላትን የማካተቱ ስራ ትኩረት ተሰጠቶ እንዲሰራ የውሳኔ
አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡
ቀጥሎ ለጠቅላላ ጉባዔው የጽ/ቤቱ የ2021 ሪፖርት በክትትልና ምዘና መምሪያ ሃላፊው
በአቶ በላይ ረታ የቀረበ ሲሆን ፤ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ በላይ
ማብራሪያ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ከ 150 ሺህ በላይ ለሆኑ ቫይረሱ በደማቸው ላለባቸው
ወገኖች በጸረ ኤች ኤቪ ህክምና ቁርኝት፤ በቫይረስ መጠን ልኬት ፤ በጸረ ኤች አይቪ ህክምና
ቅድመ ዝግጅት፤ ቤተሰብና የጾታ አጋሮቻቸውን በማስመርመር ፤ ከኮቪድ 19 በመከላከል እና
በአጠቃላይ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ድጋፍ እንደተሰጣቸው ተብራርቷል፡፡
ከቀረበው ሪፖርት መረዳት እንደተቻለውም ድርጅቱ በኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነስ እና
መድሎና መገለል እንዲቀንስ በማድረግ እንዲሁም ከጸረ ኤች አይቪ መድሃኒት ጋር ያለውን
ቁርኝት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡
አባላቱ ሪፖረቱ ካደመጡ በኋላም ፈንድ ለማግኘት ከመንግስት ጋር ያለው ቁርኝት ምን
ይመስላል፤ እንዲሁም የኔፕ ፕላስ የ 5 አመት መሪ እቅድ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ የሚሉና
የመሳሰሉ ጥቄዎችን አንስተዋል፡፡ ለጥያቄዎቹም ከድርጅቱ ጽ/በት ማብራሪያዎች
ተሰጥተዋለ፡፡
በተጨማሪም የኔፕ ፕላስ የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተገምግሞ መጠናቀቁን
እና ሴቶችና ሴቶች ጥምረትን ለማገዝ በጽ/ቤቱ በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም
ተብራርቷል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ጠቅላላ ጉባዔው የ2022 እቅድን ያደመጠ ሲሆን አባላቱም ግሎባል ፈንድ
ፈጻሚ ያልሆኑ አባላት ጉዳይ በእቅዱ ቢካተት፤ በጦርነት የተጎዱ ማህበራትና ሴቶች በተለየ
መልኩ የሚደገፉበት መንገድ ቢመቻች በማለት አሳስበዋል፡፡ጠቅላላ ጉባዔው ሪፖረቱንና
እቅዱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባዔው የ2021 የውጭ ኦዲት
ሪፖረተን ካደመጠ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡