ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭሰ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) በመድሎና ማግለል ላይ
ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጋር ውይይት አካሄደ
ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ) በኤች
አይ ቪ ምክንያት በሚደርሰው አድሎና ማግለል ላይ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ
ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴጋር ነሃሴ 2 ቀን 2014 በቢሾቱ ኪሎሌ ሆቴል ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይም የተለያዩ አካላት ንግግር አድርገዋል፡፡


የውይይቱ ተሳታፊዎች በከፊል

በውይይቱ ቋሚ ኮሚቴውን በመወከል ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ሲሆኑ፤
እሳቸውም በገለጻቸው በኤች አይ ቪ ተጽእኖ ላይ እንዲህ አይነት በቁጥር ላይ የተመሰረተ
ጥናት መቅረቡ በጉዳዩ ላይ የበለጠ ስራዎችን ለመስራት የሚኖረው ጠቀሜታ የላቀ መሆኑን
አብራርተዋል፡፡ በግምት ብቻ የሚሰሩ ስራዎች የተፈለገውን ውጤትለማስገኘትም ሆን
በህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል
ብለዋል ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ፡፡ በዚህ መልኩ ተጨባጭነት ያለው ጥናት መደረጉ በጉዳዩ
ላይ የበለጠ ለመስራት የሚፈልግ ሌላ አካል እንኳን ቢኖር ጥሩ መነሻ የሚሆንና
በማህበረሰቡ ውስጥም ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑን ወ/ሮ ወርቅሰሙ ጨምረው
ገልጸዋል፡፡


ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ
ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወክለው የመጡት ወ/ ሮ ምርቴ ጌታቸው በበኩላቸው ሚኒስቴር
መስሪያ ቤቱ የኤች አይ ቪ ስርጭት አና የሚከሰቱት ተያያዥ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ
ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ እንዲህ አይነት ጥናቶች መካሄዳቸው ስራውን የበለጠ
ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል፡፡ ባለፉት አመታት በኤች አይ ቪ
ምክንያት የሚከሰት ሞትን በ 53በመቶ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት 87 በመቶ መቀነስ
ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ምርቴ፤ የኤች አይ ቪ ህክምና ሽፋኑ 93 በመቶ እንዲሁም ቫይረሱን
የመቆጣጠር አቅም ወደ 96 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ተወካዩዋ፡፡ ተመርምሮ
ራስን ማወቅን በተመለከተም በአሁኑ ወቅት 84 በመቶ የሚሆኑት ወገኖች ተመርምረው
ውጤታቸውን ያወቁ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ 16 በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ ምክንያቶች
ምርመራ እንዳላደረጉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ተመርምረው ራሳቸውን እንዳያውቁ
ከሚያደርጓቸው ምክንያያቶች መካከልም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊደርስባቸው
የሚቸለውን መድሎና መገለል በመፍራት መሆኑንም አብራርተዋል ፡፡ በአሁኑ ሰአትም ከ
1500 በላይ የሚሆኑ የኤች አይ ቪ ህክምና መስጫ ጣቢያዎች እንዲሁም ከ4000 በላይ የ
ኤች አይ ቪ የምርመራ ጣቢያዎች እንዳሉም አብራርተዋል ወ/ሮ ምርቴ፡፡


ወ/ሮ ምርቴ ጌታቸው

እንግዶች ያደረጉትን ንግግር ተከትሎም የጥናቱን አስፈላጊነት፤ አላማ እና አካሄድ
በተመለከተ የኔፕ ፕላስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የጥናቱ የቴክኒክ ኮሞቴ ሰብሳቢ አቶ
ጌታቸው ጎንፋ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ጥናቱን ማድረግ የተፈለገበት
ምክንያት በኤች አይ ቪ ምክንያት የሚደርስ መድሎና መገለል ያለበትን ደረጃ አና ሁኔታ
ለማውቅ ፤ በመድሎና መገለል እና በኤች አይ ቪ አገልግሎት መካከል ስላለው ግንኙነት
ለመገምገም እንዲሁም በመድሎና መገለል ምክንያት የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽእኖ ማቃለል
በሚቻልበት ሁንታ ላይ ምክረ ሃሳብ ለማስቀመጥ እንደሆነ አቶ ጌታቸው በገለጻቸው
ጠቁመዋል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱን ለማድረግም የተለያዩ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮ እንደነበረ እንዲሁም
በሂደቱ የተለያዩ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ዘዴዎች መከተላቸውን ገልጸዋል፡፡ ጥናቱ
ደረጃውን የጠበቀ እና ተአማኒነት ያለው እንዲሆንም በዘርፉ ልምድ ያላቸው የጥናት ተቋማት
ያስቀመጧቸውን ያሰራር ሂደቶች በመመልከት እና በመከተል መሰራቱም በመድረኩ
ጨምረው አብራርተዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ጎንፋ
በመቀጠልም የጥናቱ ቴከኒካል ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩዬ
ዳመጠው አጠቃላይ የጥናቱን ውጤት ጠቅለል ባለ መልኩ አቅርበዋል፡፡ በማብራሪያቸወም
ከጠናቱ ተሳታፊዎች መካከል ምን ያህሉ የኤች አይ ቪ ውጤታቸውን ለሌሎች አካላት
አሳውቀዋል በሚል የጀመረው የወ/ሮ ጥሩዬ ገለጻ፤ በዚህ ጥናት ላይ ከተሳተፉ ሰዎች መካክል
84 በመቶዎቹ የኤች አይ ቪ ውጤታቸውን ቢያንስ በአካባቢያቸው ለሚገኝ አንድ ሰው
መግለጻቸውን ያመለክታል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 16 በመቶ የሚሆኑት የኤች አይ ቪ
ውጤታቸውን ለማንም ሰው ያልገለጹ መሆናቸውን ምክትል ሰብሳቢዋ አክለው ገልጸዋለ፤፡፡
በተጨማሪም 23.4 በመቶዎቹ የጥናቱ ተሳታፊዎች የ ኤች አይ ቪ ውጤታቸው
ያለፍቃዳቸው የተገለጸባቸው ፤ 19.7 በመቶዎቹ ደግሞ የ ኤች አይ ቪ ውጤታቸውን
ያሳወቁት በተለያዩ ምክንያቶች ተገደው እንደሆነ የጥናቱ ተሳታፊዎች መግለጻቸውን
አብራርተዋል፡፡ ውጤታቸውን ይፋ እንዲያደርጉ ያሰገደዷቸው ነገሮችም የፍቅር እና የትዳር
ጓደኛ ለመያዝ፤ የተለያዩ እገዛዎችን ለማግኘት አና ለመሳሰሉት ምክንያት እንደሆነ የጥናቱ
ተሳታፊዎች አብራርተዋለ፡፡

ወ/ሮ ጥሩዬ ዳምጠው
የቀረበው መረጃ እንደሚጠቁመው በ ኤች አይ ቪ ምክንያት የሚመጣ መድሎና
መገለል ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ዜጎች ላይ አዎንታዊ አና አሉታዊ ተጽእኖዎችን
ያስከትላል፡፡ 45 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹትም በኤች አይ ቪ
ውጤታቸው ምክንያት የደረሰባቸው መድሎና መገለል በሕይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ
አሳደሮባቸዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደገለጹትም በተደረገባቸው መድሎና መገለል ሳቢያ በራስ
መተማመናቸውን እንዲያጡ፤ ጭንቀትን መቋቋም እንዲያቅታቸው ብሎም የፍቅር ጓደኛ
እንኳን መያዝ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ልጅ ለመውለድ
የነበራቸውን ተስፋ እንዳሳጣቸው ገልጸዋል ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 44 በመቶ
የሚሆኑት ተሳታፊዎች በ ኤች አ ይ ቪ ውጤታቸው ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው
መድሎና መገለል የበለጠ በራሳቸው አንዲተማመኑ በማድረግ፤ ጭንቀታቸውን እንዲቋቋሙ
በማገዝ እንዲሁም ጠንካራና ተስፈኛ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ በአዎንታዊ መንገድ
እንደረዳቸው ተጠቁሟል፡፡
የጥናት ውጤቱ አጠቃላይ ዳሰሳ ከቀረበ በኋላም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አና
አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፤ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያዎች ከአቅራቢዎች
ተሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ተሳታፊዎች የየራሳቸውን አስተያያት አና ጥቆማ በመስጠት እና
ሰፊ ውይይት በማድረግ የውይይት መድረኩ ተጠቃሏል፡፡