የኤች አይ ቪ ስርጭትን በመግታት እቅስቃሴ ውስጥ ላለፉት 11 አመታት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የነበሩት ኬዝ ማናጀሮች እና የአድሄረንስ ሰፖርተሮች አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ዎርክሾፕ በቢሾፍቱ ከተማ ከመስከረም 10 – 11 ቀን፤ 2015 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፤ በውይይቱ መጨረሻም ሰራተኞቹም በመንግስት አስተዳደር ኮሚሽን እንዲታቀፉ ሃሳብ ቀርቀቧል፡፡ በዎርክሾፑ ላይም የኔፕ ፕላስ ቦርድ አባላት ፤የፌድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተወካዮች ፣ የጤና መድህን አገልግሎት ባለሞያዎች ፤ የጤና ሚኒሰቴር ተወካዮች ፤ የክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተወካዮች፤ የየክልል ጤና ቢሮዎች ተወካዮች፤ አንዲሁም የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል፡፡


የዎርክሾፑ ተሳታፊዎች በከፊል
በዎርክሾፑ መክፈቻ ላይ የኔፕፕላስ ተ/ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ጫላ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸውም ኔፕፕላስ ባለፉት 11 አመታት ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለባቸውን ዜጎች በማሰማራት በተለያየ መልኩ ህብረተሰቡን የጠቀመ መሆኑን አስረድተው፤ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ለምሳሌ የሚቀርቡ ናቸው ብለዋል፡፡ አሁንም ሲዲሲ ለዚህ ስራ ይሰጠን የነበረው በጀት ቢያቆምም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አቶ ባይሳ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

በአሁን ወቅት በሃገሪቱ ያለውን የኤች አይ ቪ ሁሄታ በተመለከተ የጤና ሚኒሰቴርን ወክለው ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ ደስታ ሞገስ ሲሆኑ፤ በጽሁፋቸውም በየአመቱ ከ 1ነጥነብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ምክንያትም 680 ሺ ዜጎች ህይወታቸው ያልፋል ብለዋል፡፡ በቀረበው ጽሁፍ እንደተቀመጠው ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ሲሆኑ፤ በዚህም መሰረት 19 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሴቶች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኘ ተገልጿል፡፡ የወንዶችን ቁጥር ስንመለከት ደግሞ 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን ወንዶች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፤ እንደ ጽሁፉ፡፡ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ምክንያት የሚሞቱ ወገኖች ቁጥርን ስንመለከትም በቀላሉ የሚታይ አይደለም ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚሁ ምክንያት በየአመቱ 640ሺ ወንዶች እና 240 ሴቶች ህይወታቸው ያልፋል ብለዋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት በእድሜ ስብጥር ስንመለከተው በ2021 በነበረው መረጃ መሰረት በየአመቱ አድሜያቸው ከዜሮ እስከ 14 አመት የሆነ 150 ሺ ህጻናትና ታዳጊዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ሳቢያም 99ሺ ሕጻናትና ታዳዎች በሞት ይቀጠፋሉ፡፡ በክልል ደረጃ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት በተመለከተም መረጃው እንዳስቀመጠው በ2021 አማራ ክልል፤ ኦሮሚያ እንዲሁም አዲሰ አበባ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ካደረጉት ምክንያቶች መካከልም በተለይ ሴቶች ስለቫይረሱ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤ ኮንዶምን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ጾታን መሰረት ያደረጉ ተግባራት አሁንም ድረስ እየተተገበሩ መሆኑ እንዲሁም የወሲብ ንግድ መስፋፋት ናቸው፡፡
የአቶ ደስታን ማብራሪያ ተከትሎ የኔፕፕላስ ፐሮገራም ማናጀር አቶ ድንቁ ወርቁ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ምንነት እና አስፈላጊነት የሚገልጽ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ በጽሁፋቸውም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በጤና ተቋማት እና በማህበረሰቡ መካከል የሚኖረው አገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በማህበረሰቡ እና በጤና ተቋማት ዘንድ ያለውን ሀብት በአግባቡ አሟጦ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ አብራርተዋል፡፡ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ዋና ዋናዎችም ዜጎች የኤች አይ ቪ ምርመራ እንዲያደርጉ የምክር አገልግሎት መስጠት ፤ ከራሳቸው ተሞክሮ ተነስተው ያለውን ሁኔታ በግልጽ በማስረዳት ቫይረሱ በደማቸው ያለ ዜጎች ህክምና እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም ህክምናውን ያቋረጡ ዜጎች ወደ ህክምናው እንዲመለሱ የተለያዩ ጥረቶችን ማድረግ ተጠቃሾች መኆናቸን አቶ ድንቁ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

የዎርክሾፑ አወያዮች

ሌላው የኬዝ ማናጀሮችና ደሄረንስ ሰፖረተሮች ስራ ያስገኛቸው ውጤቶችና የጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ጽሁፍ ያቀረቡት የኔፕፐላስ ምዘናና ግምገማ ባለሞያ አቶ ቢኒያም ወርቁ ሲሆኑ፤ በጽሁፋቸውም ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሚሰሯቸው ስራዎች በርካቶች ቫይረሱ በደማቸው ያለ ዜጎች ህክምናቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እና ህክምና ባለማግኘታች ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን ማስቀረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ለአብነት ያህልም በ2020 እና በ2012 ብቻ ህክምናቸውን ካቋረጡ ከ80ሺ በላይ ወገኖች መካከል ከ40ሺ በላይ የሚሆኑት ወደ ህክምና እንዲመለሱ ማድረግ ችለዋል ብለዋል አቶ ቢኒያም ፡፡በተጨማሪም በኬዝ ማናጀሮች እገዛ እየተደረገላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸው የኤች አይ ቪ ምርምራ እንዲያደርጉ በማሳመን እና ወደ ምርመራ ቦታ በማምጣት ሥራው ላይ እንዲሳተፉ ማድረጋቸውን አቶ ቢኒያም በማብራሪያቸው ገልጸዋል፡፡
የኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖረትሮች የሚሰጡት አገልግሎት በርካታ ቢሆንም፤ ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ የሚደርጓቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸውንም አቶ ቢኒያም አስረግተዋል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች መካከልን እንደ እሳቸው ገለጻ ዋና ዋናዎቹ የምክክር አገሎገሎት ለመስጠት የሚመቹ ገለልተኛ ክፍሎች አለመኖር፤ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰርቪስ ስር ባለመታቀፋቸው ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች ማግኘት አለመቻላቸው፤ ከጤና ተቋማት ደጋፍ በተገቢው መንገድ ማግኘት ነጻ ህኪምና ማግኘት አለመቻላቸው እንዲሁም ዝቅተና ደመወዝ ተከፋይ መሆናቸው እና የፕሮጀከቶች ስራ በጊዜ የተገደበ መሆን ተጠቃሾቹ ናቸው ብሏል አቶ ቢኒያም፡፡
ከየተቋማቱ የመጡ ተሳታፊዎች በየዘርፋቸው 20 የደቂቃ ገለጻዎችን ያደረጉ ሲሆን፤ በዋናነት ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮችም የኤች አይ ቪ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ፤ የኬዝ ማናጀሮች አስፈላጊነት፤ የሚሰሯቸው ስራዎች አንዲሁም ስራዎቻቸውን በሚሰሩበት ወቅት የሚገጥሟቸው ችግሮች አና ችግሮቹን ለመፍታት የተጓዙባቸውን መንገዶች የሚያስረዱ መረጃዎች ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠልም እያንዳንዱ ክልል የየራሱን ተሞከሮ ያቀረበ ሲሆን፤ የአማራ ክልል ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰርቪስ ስር እንዲካከቱ በማድረጉ ችግሩን ከሞላ ጎደል መቅረፍ መቻላቸውን ተወካዩ አስረድተዋል፡፡ ሌሎችም በቀጣይነት ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች በሲቪል ሰረቪሱ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በጤና መድህን ሊታቀፉ የሚችሉበት እና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት በሚቻልበት መንገድ ላይም ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ ከኢትጵያ ጤና መድን አገልግሎት ተወካይ አቶ ጉደታ አበበ በአሁኑ ወቅት ያለውን የጤና መድን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ እንደ አቶ ጉደታ ማብራሪያ የጤና መድን አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ መዳረሱ እንደ ግዴታ ሊወሰድ ስለሆነ ማንም ከዚህ አገልግሎት ውጪ ሊሆን አይችል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉም ዜጋ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አሊያም በማህበራዊ ጤና መድህን እንዲታቀፍ የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ሥለሚደረግ በዚህ ሂደት ውስጥ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ዜጎችም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አቶ ጉደታ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በተለይ ኬዝ ማናጀሮችና አድሄረንስ ሰፖርተሮች የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ረገድ ያላቸው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ በሲቪል ሰርቪሰና በጤና መድን ስር ታቅፈው አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ እና እያንዳንዱም የየራሱን ሃላፊነት ለመወጣት ቃል በመግባት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡