ኔትዎርክ ኦፍ ኔትዎርክስ ኦፍ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭሰ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕፕላስ)  ከጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 16 ቀን  2016 በአዳማ ከተማ ካኖፒ ሆቴል ባካሄደው  የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት የግምገማ መርሃ ግብር እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 ቀን 2023 እስከ ዲሴምበር  31 ቀን  2023 ባለው ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት እና               የፋይናንስ አፈጻጻም ተገምግሟል፡፡ ከአፋር  ክልል ውጪ ሁሉም ክልሎች አፈጻጸማቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ የሪፖርቱ ይዘትም የተከናወኑ ተግባራት፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተመዘገቡ መልካም ወጤቶች  እንዲሁም የመፍተሄ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

የግምገማው ተሳታፊዎች በከፊል

በአሁን ወቅት ከ110 በላይ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች እንሚገኙበት በሚታወቀው አዲስ አበባ
ከተማ ስራውን በመስራት ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ማህበራት
ጥምረት (አኖፓ) በአፈጻጸም ረገድ ያሉትን መልካም ተሞክሮዎች ያቀረበ ሲሆን፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አያሌ
ተግዳሮቶች እንደገጠሙትም አልሸሸገም፡፡ ጥምረቱ ከህክምና የጠፉ ታካሚዎችን አፈላልጎ በመመለስ፤
ቫይረሱ በደማቸው ላለ ወገኖች የስራ እድል መፍጠር እና ቫረሱ በደማቸው ለሚግባቸው ለተማሪዎች ወደ
ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ መድሃኒት በሚገኝበት አካባቢ እንዲመደቡ በማድረግ ረገድ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን
ገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በፈቃደኝነት እንዲያደርጉ እና ህክምና እንዲያገኙ
እንዲሁም የምግብ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረጉን በሪፖርቱ አስቀምጧል፡፡

ተሰባሳቢዎች በከፊል

ጥምረቱ  እንደ ተግዳሮት ካስቀመጣቸው ጉዳዮችም መካከል በከተማዋ ላይ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የሆን አድሎማ ማግለል እየተስተዋለ መሆኑ፤ በርካታ ከህክምና የተሰወሩ ታካሚዎች አድራሻ አለመታወቁ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 119 ወረዳዎች ቢኖሩም የጤና ድርጅቶች  የሚገኙት  በ28 ወረዳዎች ብቻ መሆኑ ያሰቡትን ያህል ተገልጋይ ማግኘት አለመቻላቸው፤ እንዲሁም የሃብት እጥረት መኖሩ  ናቸው፡፡

ሌላው የአፈጻጸም ሪፖርት  ያቀረበው ኔትዎርክ የደቡብ  ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ ማህበታት ያቋቋሙት ጥምረት (NoSAHHID+ ) ነው፡፡ በክልሉ ከግሎባል ፈንድ በተገኘው በጀት የተሰሩ ስራዎች አብዛኞቹ በታሰበው እቅድ መሰረት የተከናወኑ መሆናው በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በደማቸው ውስጥ   የቫይረስ መጠን ከፍተኛ ከሆኑት  ወገኖች መካከል   53 በመቶውን መድረሳቸውን ተብራርቷል ፡፡ በደማቸው ውስጥ ያለውን ቫይረስ መጠን በሚፈለገው ደረጃ መቀነስ የቻሉትም ከታቀዱት ውስጥ  62 በመቶ መድረሱም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም ከህክምና የጠፉትን አፈላልጎ ማስመለስ የተቻለው 41 በመቶዎቹን ብቻ መሆኑ እንደ ዝቅተኛ አፈጻጸም  ቀርቧል፡፡

ጥምረቱ እንደ ተግዳሮት ያነሳቸው ጉዳዮችም መካከል  በማህበራት ደረጃ በቂ የሆነ ሰራተኛ አለመኖር፤ የጤና ተቋማት የተጠቃላች መረጃን ለመስጠት ቸልተኝነት ማሳየት እና የተዛባ መረጃ እና አድራሻ መስጠት እንዲሁም በፋይናንስ አያያዝ ላይ  የክህሎት ማነስ  ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡ ጥምረቱ በዚህ ሩብ አመት አፈጻጸሙ ውስጥ ለየት ያሉ ተግባራትን ማከናወኑን የገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም ቫይረሱ  በደማቻቸው ያለባቸው ወገኖች የጤና መድን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤ እንዲሁም ወጪዎቻቸው በተለያዩ አካላት እንዲሸፈኑ ማስቻል፤ ከተለያዩ የሰባአዊ መብት ጥበቃ አካለት ጋር በመተባበር ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች ጉዳይ የሰባአዊ መብት ገዳይ ተደርጎ እንዲወሰድ ማስወሰን እና የተለያዩ ገቢ ምንጮችን መፍጠር ተጠቃሽ ናቸው  ተብሏል፡፡

ተሰብሳቢዎች በከፊል

የአማራ ክልል ጥምረትም ሌላው  የሩብ አመቱን አፈጻጸም  ያቀረበ ጥምረት ሲሆነ፤ ጥምረቱ በሪፖርቱ ልክ እንደ ሌሎቹ ጥምረቶች ሁሉ መልካም አፈጻጸም መስገንዘቡን አስታውቋል፡፡ በተለይም ከህክምና የጠፉ ደንበኞችን ወደ ህክምና የመመለስ ስራ አፈጻጸሙ ከታቀደው በላይ ሆኖ ተግኝቷል፡፡  bzihe msrte በዚህ መሰረት ከህክምና ጠፉ ተብለው ሪፖርት ከተደረጉት 1019 በላይ 864 (84% ) ታካሚዎችን  ወደ ሀወከወመወና ማስመለስ የተቻለ ሲሆን፤ 103 እምቢተኞች ነበሩ፡፡ የተቀሩት 6  በመቶ  የሆኑት ደግሞ  ከህክመና የጠፉ፤ ህይዌቸውን ያጡ እንዲሁም በገዛ ፍቃዳቸው ወደ ሌላ የህክምና አገልግሎት የተዛወሩ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ  ሰዎች ኤ አይ ቪ በደማቸው መኖር አለመኖሩን ተመርምረው  ራሳቸውን እንዲያውቁ የማድረግ ስራም ከታቀደው እቅድ በላይ ተፈጽሞ  ተመዝግቧል፡፡ በዚሁ መሰረት820 ሰዎችን ለመመርመር ታቅዶ 1004 ሰዎች ከእቅድ በላይ ለመመርመር ተችሏል፡፡ በአጥቃላይም አዲስ ምርመራ የሚደርጉ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻቸው ቁጥር፤ ከህክምና የጠሰወሩትን አፈላል የማግኘት እንዲሁም ወደ ህክምና የመመለስ ስራዎች እንዲሁም ከጤና ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ስራዎች ላይ ከባለፈው ሩብ አመት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ተግልጿል፡፡

ክልሉ ሌላኛው የእርስበርስ ጦርነት ተጠቂ እንደመሆኑ  በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ  ማለፉን አስቀምጧል፡፡ በዚህም ሳቢያ 24 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ ተገልጿል፡፡ ጥምረቱ ተግባራን በሚያከናውንበት ወቅት እንደ ተግዳሮት ያስቀመጣቸውም ጉዳዮች አስቀምጠዋል፡፡ የመጀመሪያው ተግዳሮትም  የሃገር ውስጥ ሃብት ለማፈላለግ ጥረት አለማድረግ፣ በቂ እና በአግባቡ የተያዘ  ዳታ አለመኖር፣ የኮንዶም  እና የመመርመሪያ  መሳሪያ እጥረት ፣ ከጤና ተቋማት ጋር ለመተሳሰር ፈቃደኛ አለመሆን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም ክልሎችም  በተመሳሳይ ደረጃ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መኆኑን ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፤ ይሐው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመስማማት ግምገማው ተጠናቋል፡፡